🔒የSocial Media አካውንቶቻችንን ደህንነት እንዴት ማስጠበቅ እንችላለን?🔒
አብዛኞቻችን ቢያንስ ሁለት ሶስት የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችን የተለያዩ መሰል አገልግሎት የሚሰጡ መተግበሪያዎች ላይ ለግል ጉዳይም ይሁን ለስራ ከፍተን እንጠቀማለን ፤ ለምሳሌ፡ Facebook ,
Telegram , WhatsApp , Tiktok , SnapChat , Tumblur, Discord, Viber , imo ,Wechat, Instagram እና ሌሎችም ላይ እንደየ ምርጫችን አካውንት ከፍተን እንጠቀማለን ።
እነኚህ ፕላትፎርሞች ላይ የግል መረጃችንን አስገብተን ስንጠቀም ለጥቃት እንዳንጋለጥ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባናል ፤ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንታችን ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ የሚከተሉትን እርምጃዎች
መውሰድ ይገባናል ፤
1. ጠንካራ ና በቀላሉ የማይገመት የይለፍ ቃል ወይም ፓስወርድ መጠቀም /Strong password
የይለፍ ቃላችን ጠንከር ያለ ና ቢያንስ ከስምንት ካራክተር ያላነሰ እንዲሁም upper case Letters , Lower case letters , special characters ሊኖረው ይገባል።ፓስወርዳችን
ርዝመቱ በጨመረ ቁጥር በቀላሉ crack አይደረግም። ፓስወርዳችንን በፍጹም ስማችን ወይም ሌሎች በቀላሉ ሊገምቷቸው የሚችሏቸውን ቃላት ማድረግ የለብንም ፤ ወረቀት ላይም ጽፈን ማስቀመጥ የለብንም ፤
ማስታወስ ይኖርብናል! ፓስወርዳችንን በተወሰነ ግዜ ውስጥ መቀየርም ይመከራል ።
2. ለሁሉም አንድ አይነት ፓስወርድ መጠቀም የለብንም / Use Unique Password for each
ለሁሉም ሶሻል ሚዲያ አካውንቶች አንድ አይነት ፓስወርድ መጠቀም ለግዜው ህይወትን ያቀለለ ቢመስለንም ፤ ችግር ካጋጠመን ግን ሁሉም ተጋላጭ ይሆናሉ። ስለዚህ ለሁሉም የተለያየ ፓስወርድ ነው
መጠቀም ያለብን። ለማስታወስ ከባድ ቢሆንም ለደህንነት ግን ተመራጭ ነው።
3. ኮምፒውተራችን ላይ ወይም ስልካችን ላይ ፓስወርድ አለማስቀመጥ /Don't Save passwords
አንዳንዴ Login ለማድረግ ፓስወርድ ካስገባን በኋላ ላስቀምጥላችሁ ወይ የሚል ጥያቄ ይጠይቀናል ፤ ያኔ አይሆንም ማላት አለብን ፤ በተለይ ብዙ ሰው የሚጠቀምበት ኮምፒውተር ወይም ስልክ ላይ ከሆነ
ጥንቃቄ ያስፈልጋል ፤ ፓስወርድ አስቀመጥን/save አደረግን ማለት ፤ ከዚያ በኋላ እዚያ ዲቫዝ ላይ ስንከፍተው ፓስዎርድ አይጠይቅም ማለት ነው ። ለምሳሌ፡ የፌስቡክ ፓስወርዳችንን አንድ ኮምፒውተር ላይ
Save አድርገን ከሆነ ከዚያ በኋል ማንም ሰው መጥቶ Facebook.com ብሎ ፔጁን ቢከፍት በቀጥታ የኛውን ፌስቡክ አካውንት ነው የሚከፍተው ፤ ያለ ምንም ፓስወርድ ! ስለዚህ ጥንቃቄ
ያስፈልጋል።
4. Two factor Authenticationን ማብራት / ኦን አድርጎ መጠቀም
Two factor authentication የምንለው ፤ ከፓስወርድ በተጨማሪ አካውንታችንን ለማጠንከር የምንጠቀምበት ነው ፤ ይህ ማለት ሰዎች ፓስወርዳችንን ቢያገኙትም ከአዲስ ዲቫይዝ ላይ እንዲሁም
ተመሳሳይ ዲቫይዝ እንኳን ቢሆን አዲስ ብራውዘር ከተጠቀምን ከፓስወድ በተጨማሪ ሌላ ማጠንከሪያ ይፈልጋል ፤ ለምሳሌ ፡ በስልክ ፣ በኢሜይል ኮድ ልኮ እኛ መሆናችንን ያረጋግጣል ወይም እኛ ብቻ በምናውቀው
ሴኩሪቲ ጥያቄ ያረጋግጣል ። ሁሉም ማህበራዊ ሚዲያዎች ይህ ፊቸር ይኖራቸዋል ስለዚህ እሱን አብርተን ብንጠቀም ይመከራል።
5. የሁሉንም ሶሻል ሚዲያ አፖች Privacy Setting እያየን ማስተካከል
ሁሉም የራሳቸው የሆነ የግላዊነት መደላድል / Privacy Setting አላቸው ያንን እያየን ክፍተቶችን መድፈን ያስፈልጋል።ለምሳሌ፡ Telegram ላይ ብናይ Privacy Setting ውስጥ ስንገባ ኦንላይን
መሆናችንን ማሳወቅ ወይም መደበቅ ፣ ስልክ ቁጥራችንን ማን ማየት እንዳለበት ፣ ፕሮፋይል ምስል ማየት ያለባቸው እነማን እንደሆኑ ፣ ግሩፕ ላይ አድ እንድንደረግ መፍቀድ ወይም መከልከል ና ሌሎችንም
መወሰን እንችላለን።
6. ከማናውቃቸው ሰዎች የሚመጡልንን Friend requests ወይም መልዕክቶች በጥንቃቄ ማየት
ምንም ከማናውቃቸው ና እንደ ጓደኛ አድ ካላደረግናቸው ሰዎች የሚመጡ ድንገተኛ መልዕክቶችን ወይም friend requests ቆም ብሎ ማሰብ ያስገልጋል ፤ በተለይ የሚላክልን መልዕክት ላይ ሊንኮች /
ማስፈንጠርያዎች ካሉ ክሊክ ከማድረጋችን በፊት ምንድ ነው ? ከየት ነው? ማነው? የሚለውን ማጣራት ብልህነት ነው።
7. መተግበሪያዎችን ቶሎ ቶሎ ማዘመን / Update ማድረግ
አዳዲስ ማዘመኛዎች ተጨማሪ ፊቸሮችን ይዘው ከመምጣታቸም በላይ ፤ መተግበሪያዎቹ ላይ ለሚታዩ የደህንነት ክፍተቶች መፍትሄ ይዘው ይመጣሉ ስለዚህ ማዘመኛዎች ካሉ በወቅቱ update ማድረግ አለብን።
8. ሁሌም ተጠቅመን ስንጨርስ Logout ማድረግ
ማንኛውንም የሶሻል ሚዲያ አካውንት ተጠቅመን ስናበቃ ክፍቱን ከመተው መዝጋት / Logout ማድረግ ይመከራል።
9. ኦን ላይን ስለራሳችን በጣም ዝርዝር መረጃ ከመስጠት መቆጠብ/avoid sharing detail personal information online
አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ዝርዝር ግላዊ መረጃችንን አለ መስጠት ፤ ጠላፊዎች የግል መረጃችንን በዝርዝር ካገኙ Social Engineering ለሚባል የሳይበር ጥቃት ተጋላጭ ልንሆን እንችላለን።
10. ባልተገባ መልኩ ሊያግባቡን የሚሞክሩ ካሉ ና ጥርጣሬ ካለን ብሎክ ማድረግ