በጣም ጠቃሚ ና አስፈላጊ ዌብሳይቶችን እንጠቁማችሁ!
1. Edx
በ2012 በHarvard University ና MIT(Massachusetts Institute of Technology) የተመሰረተ ሲሆን አሉ ከሚባሉ ትምህርታዊ ድረ ገጾች ውስጥ ይመደባል።
በነጻ ና በክፍያ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ና ሌሎች ኮርሶችንም ከታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች በኦንላይን መከታተል ያስችለናል።
2.Mayo Clinic
በአሜሪካ የሚገኝ በጣም ታዋቂ ሆስፒታል ሲሆን ፤ በድረገጹ ላይ ማንኛውንም ጤና ነክ መረጃ በጣም በተብራራ መልኩ እናገኝበታለን።
3.
Bleepig Cmputer
ማንኛውንም ኮምፒውተር ነክ መረጃዎችን ወይም ጥያቄዎችን መረጃ ያገኙበታል ፤ ቴክ ወሬ ፤ ቫይረስ removal Guide ፣ ሶፍትዌሮችን እንዲሁም ሌሎች ቴክኖሎጂ መረጃዎችን ያገኙበታል።
4.
Extends Class
ለሶፍትዌር ዲቨሎፐሮች የሚሆኑ ና ስራን የሚያቀሉ የተለያዩ ቱሎችን የያዘ ዌብሳይት ነው ለምሳሌ፡ Code tester , Code formater , syntax validator , Mock server(መሞከርያ ቨርቿል ሰርቨሮች ) ና ሌሎችም በርካታ የSoftware development tools ለተለያዩ Programming ና Scripting Languages ይዟል ተጠቀሙበት።
5.
faxzero
Faxzero የኢሜይል አድራሻችንን በመጠቀም ፋክስ ማሽን መጠቀም ሳያስፈልገን በነጻ fax መልዕክት መላክ ና መቀበል ያስችላል።
6.
About.me (https://about.me/)
Personal ዌብሳይት በ .me ዶሜን በነጻ ማዘጋጀት ከፈለጋችሁ ይህን ሞክሩት ።
7.
cleanpng(https://cleanpng.com)
ለተለያዩ ጉዳዮች ባክግራውንድ የሌላቸው የተለያዩ ምስሎችን በነጻ ማግኘት ስንፈልግ ፤ የምንፈልገውን ሰርች አድርገን ዳውንሎድ ማድረግ እንችላለን።
8.
privnote ( https://privenote.com )
በኢሜይል ና በሌሎች አማራጮች የምንልከው መልዕክት አንዴ ከላክነው ፤ የተላከለት ሰው ካላጠፋው በቀር ሁሌም ይኖራል ፤ ነገር ግን በኢሜይል የምንልከው መልዕክት ከተነበበ በኋላ self destruct
እንዲያደርግ ወይም በሰጠነው ግዜ መሰረት እንዲጠፋ ከፈለግን ይሄን ድረገጽ ልንጠቀምበት እንችላለን። ልክ ቴሌግራም ላይ እንዳለው ሰልፍ ዲስትራክት መልክት መላኪያ ፊቸር መልዕክቱ ከተላከ ና ከተነበበ በኋላ ይጠፋል።
9.
Down for Everyone or Just Me/https://DownforEveryoneorJustMe.com
አንዳንዴ የተለያዩ ድረገጾችን ለመክፈት ስንሞክር አልሰራ ካለን ችግሩ ለኛ ብቻ ነው ወይስ ለሁሉም ነው የሚለውን ለማረጋገጥ ይሄን ድረገጽ ከፍተን እምቢ ያለንን ሳይት url ብናስገባለት ቼክ አድርጎ ያሳውቀናል። የዚህ ዌብሳይት url ረጅም ከሆነባችሁ ፡ downfor.io የሚልውን መጠቀም ይቻላል። 10.
Educations.com / https://www.educations.com
ይህ ዌብሳይት በተለያዩ የትምህርት ደረጃዎች ዲግሪ ና ማስተርስ እንዲሁም አጫጭር ኮርሶችን ከተለያዩ ሃገራት ከአፍሪካ ፣ አውሮፓ ና አሜሪካን ጨምሮ በሁሉም መስክ እንደየ ፍላጎታችን በርቀት ፣ በአካል
መርጠን መማር ስንፈልግ ልንጠቀምበት እንችላለን። ብዙ ፊልተር ማድረጊያ መንግዶች ስላሉት በቀላሉ የምንፈልገውን የትምህርት አይነት ማግኘት እንችላለን።
#Deritatech #mostusefullwebsites #TechTips #bestwebsites #Techtipsandtricks