Showing posts with label How to buy SMartphones. Show all posts
Showing posts with label How to buy SMartphones. Show all posts

ስልክ ስንገዛ ማየት ያለብን ዋና ዋና ነገሮች! | Smartphone Buying Guide | How to Buy Smartphones-Amharic


ስልክ ስንገዛ ማየት ያለብን ዋና ዋና ነገሮች!

አዲስም ይሁን ያገለገለ ስልክ በተለይ እስማርት ስልክ ስንገዛ አቅማችንን ባገናዘበ መልኩ የሚከተሉትን ነገሮች ከግምት አስገብተን ብንገዛ ስልካችን በተሻለ መልኩ ሊጠቅመን ይችላል! ስልክ ለመግዛት ስናስብ መጀመሪያ የያዘነውን በጀት ባገናዘበ መልኩ የስልኩን Specification / ስልኩ ምን ምን ነገሮች እንዳሉት ወይም ምን ምን ገጽታዎች እንዳሉት ማየት አስፈላጊ ነው ፤ የስልኩ ስፔሲፊኬሽን ላይ ሁሌም ከማይጠፉ ና እኛም ሁሌ ማየት ያለብንን ነገሮች የተወሰኑትን እን መልከት፤


📷

ካሜራ


አሁን ላይ ስልክ ስንገዛ አብዛኞቻችን ቅድምያ የምናየው ና ማየትም ያለብን ካሜራውን ነው ፤ ምክንያቱም ስማርት ስልክ መጠቀም ከጀመርን ወዲህ ሌላ ተጨማሪ ካሜራ መያዝ ትተናል ስለዚህ ስልካችን ጥሩ ካሜራ ካለው ለትውስታም ይሁን ለማስረጃ ማስቀረት የፈለግነውን ነገር ማንሳት እንድንችል አቅምን ባገናዘበ መልኩ ጥሩ ካሜራ ያስፈልገናል፤ የአንድ ስልክ የካሜራው ጥራት ለማወቅ በርካታ ነገሮች ቢታዮም በዋናነት ግን የስልኩ ካሜራ MegaPixel / MP መታየት አለበት ፤ ይህ በካሜራው የሚነሳውን ፎቶ ጥራት የሚወስን ነው ፤ ከፍያለ ሜጋ ፒክስል ያለው ካሜራ ወይም ስልክ የተሻለ ጥራት ያለው ፎቶ ያነሳል።


💾

Internal Storage


ይህ ስልካችን ሚሞሪ ካርድ ሳንጠቀም ፤ ምን ያህል ዳታ እንደሚይዝልን የሚወስን ነው ፤ ስልካችን ሚሞሪ ካርድ ስሎት ከሌለው ይህ ከፍ ያለ ቢሆን ይመከራል ፤ ስልካችን ሚሞሪ የሚጠቀም ከሆነ የግል መረጃችንን ወደ ሚሞሪው መውሰድ ስለ ምንችል ብዙም አሳሳቢ አይሆንም ፤ ነገር ግን ሁሌም ከፍ ያለ GB Internal Storage ቢኖረው አይከፋም።
🖌

RAM / Random Access Memory

/ ራም
ራም ለስልካችን በጣም ወሳኝ አካል ሲሆን ፤ ስልካችን ፈጣን እንዲሆን የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል ፤ ስልካችን ላይ በተለይ ጌም የምንጫወት ከሆነ ፤ ቪዲዮ ኤዲቲንግ የምን ሰራ እና ሌሎች ጠንከር ያሉ ስራዎችን የምሰራ ከሆነ ስልካችን ከፍ ያለ GB ራም ያስፈልገዋል ፤ ስለዚህ ለስካችን ከፍ ያለ GB RAM እንምረጥ ።
🟢

Processor / CPU


ፕሮሰሰር ወይም ሲፒዩ ለስካችን ልክ እንደ አንጎል ነው ፤ ማንኛውም ስልካችን የሚያከናውነው ነገር በፕሮሰሰር ትዕዛዝ የሚፈጽም ነው ፤ የፕሮሰሰር ፍጥነት በጊጋ ኸርዝ ፐር ሰከንድ/GHz/s የሚለካ ሲሆን ይሄም ኮምፒውተራችን በሰከንድ ምን ያህል ቢሊየን ትዕዛዞችን እንደሚያከናውን ይገልጻል ፤ ከፍ ያለ GHz/s ፕሮሰሰር ፍጥነት ያለውን ስልክ መምረጥ ጥሩ ነው።
🖥

Display / Screen Size ና Resolution/ጥራት


ስልኮች በተለያየ የስክሪን መጠን ና የስክሪን ሪዞሉሽን ሊመጡ ይችላሉ ፤ የስክሪን ሳይዝ እንደየፍላጎታችን የሚወሰን ሲሆን በጣም ካነሰ ለአንዳንድ ስራዎች ላይመቸን ይችላል ለምሳሌ ለማንበብያ ፤ ፎቶ ፣ ቪዲዮ ኤዲት ለማድረግ እና ለመሳሰሉት ነገሮች ከፍ ያለ ቢሆን ጥሩ ነው ፤ ነገር ግን ለአያያዝም መመቸት ስላለበት ለሁሉም ተስማሚ / ideal SCreen size ብንመርጥ ይመከራል ፤ ከ 5.5 እስከ 6 ኢንች ስክሪን ለብዙዎቻን ተስማሚ ነው ፤ የስክሪን ሪዞሉሽን ደግሞ HD , Full HD ወይም QHD/Quad High Definition (QHD) ቢሆን መልካም ነው።
🔦

Battery Life / የስልካችን የባትሪ ቆይታ


ስልካችንን እንደልብ እንድንጠቀምበት ባትሪው አስተማማኝ መሆን አለበት ፤ አዲስም ይሁን ያገለገለ ስልክ ስንገዛ Battery Capacity ማየት ይገባናል ፤ የባትሪ ካፓሲቲ በሚሊ አምፕ አወር / mAH የሚለካ ሲሆን ከፍ ያለ mAH ያለው የስልክ ባትሪ የተሻለ ቆይታ ይኖረዋል ፤ ለምሳሌ፡ ከ2000mAH ፤ 3000mAH ወይም ከዚያ በላይ ያለውን መምረጥ አለብን።
🔒

ስልኩ ያለው የደህንነት መጠበቂያ መንገዶች / Security Features


አሁን ላይ በርካታ ስልኮች ከፓተርን ና ከይለፍ ቃል ባለፈ ተጨማሪ የደህንነት ማስጠበቂያ መንገዶች አሏቸው ለምሳሌ ፡ ፊንገር ፕሪንት ሴንሰር / Finger Print Sensor ፣ የአይሪስ ሴንሰር ስካነር / Iris scanner/የአይን ብሌን ሰካነር አሏቸው ፤ finger print sensor ና iris scanner ስልካችንን እኛ ብቻ አንሎ ማድረግ እንድንችል አንዲሁም አንዳንድ ክፍያዎችን ለመክፈል እንደ ማረጋገጫ ልንጠቀምባቸው እንችላለን። ይህ ፊቸር ያላቸው ስልኮች ከሌሎቹ ስልኮች የተሻለ ደህንነት ለስልካችን ይሰጣሉ ፤ ስለዚህ ከሌለው ስልክ ያለውን መምረጥ የተሻለ ነው።
🖌

Android / IOS version / የስልካችን ስረአተክወና ወይም ኦፕሬቲንግ ሲስተም


ስልካችን ህይወት ኖሮት መጠቀም እንድንችል ፤ ከስልካችን ጋር እንደልብ መነጋገር እንድንችል ፤ ስልካችን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ያስፈልገዋል ፤ አብዛኞቹ ስልኮች Android ወይም IOS የተጫነባቸው ሲሆኑ ፤ የቅርብ ግዜ የሆኑትን አንድሮይድ ወይም አይ ኦ ኤስ መምረጥ ስልካችን ብዙ አዳዲስ ፊቸሮች እንዲኖሩት እንዲሁም ደህንንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ይረዳል።
📌

ስልኩ የተሰራበት ማቴሪያል


ስልኮቻችን ከተለያየ ነገር ሊሰሩ ይችላሉ ፤ በተለይ የውጪው ከቨር ከፕላስቲክ ፣ ከመስታወት እንዲሁም ብረትም ይኖራል ፤ ስለዚህ ስልካችን ወድቆ ሳይከፋው እንዲነሳ የተሻለውን መምረጥ ይገባል ፤ ፕላስቲክ ና ብረት ከሆነ ቢወድቅ ከተወሰነ ከፍታ ድረስ የመቁቁም አቅም አላቸው ፤ መስታወት ነክ ከሆነ አለቀለት ። የስልካችን ውጫዊ አካል ከምን እንደተሰራ ለማወቅ በስልኩ ሞዴል ኦንላይን ብንፈልግ እናገኛለን።
☎️

ስልኩ የሚሰራበት የኔትወርክ አይነት


በ1979 በጃፓን ከተዋወቀው ና ድምጽ / voice call ብቻ ከሚሰራው ከመጀመሪያው ትውልድ/1G ኔትወርክ ጀምረን 2G , 3G , 4G , 5G እያልን አሁን ላይ ስድስተኛው ትውልድ / 6G ሙከራ ላይ ይገኛል። ስለዚህ ከዘመኑ ጋር አብረን ለመጓዝ የምንገዛው ስልክ አሁን ላይ ቢያንስ 4G የሚሰራ ቢሆን በጣም ጥሩ ነው።
መልካም ንባብ!