በስራቦታ ለተለያዮ ሲስተሞች/አፖች ወይም ለ ግል ኢሜይላችን ፣ ፌስቡክ ፣ ትዊተር ፣ ሊንክድኢን ና ለሌሎችም የምንጠቀመው የይለፍቃል / ፓስወርድ ምን መምሰል አለበት?
የይለፍቃል ወይም ፓስወርድ ስንፈጥር በተቻለ መጠን ተገማች ያልሆነ ና በቀላሉ ክራክ ሊደረግ የማይችል መሆን ይኖርበታል፤ፓስወርዳችን በስማችን ወይም በሌሎች በጣም ቀላል በሆኑ ና እኛን የሚያውቁ ሰዎች በቀላሉ የሚገምቷቸው መሆን የለባቸውም።
ፓስወርዳችንን በቃላችን መያዝ ይኖርብናል ፤ ካልሆነ ግን በተገኘው ቦታ ወረቀት ላይ ለማስታወስ ብለን መጻፍ ለደህንነት ስጋት ያጋልጣል! ከዚህ በተጨማሪ የሌሎች ሠዎች ኮምፒውተር ላይ ወይም እንደ ኢንተርኔት ካፌ ያሉ ቦታዎች ላይ ስንጠቀም አልያም ከሌላ ሰው ጋር ኮምፒውተር የምንጋራ ከሆነ የኢሜይል ፣ የፌስቡክ ፣ ወይም የሌሎች ሲስተም ፓስወዶችን ብራውዘር ላይ ሴቭ ማድረግ በጭራሽ የለብንም ፤ ፓሰወርድ ሴቭ አደረግን ማለት ከኛ ውጪ የሆነ ሰው የይለፍቃል ማስገባት ሳይጠበቅበት የኛን መረጃ ሊያይ ሊበረብር ከፍ ሲልም ባልተገባ መልኩ ሊጠቀምበት ይችላል።
ሌላው አንድ አይነት ፓስወርድ ለሁሉም ሲስተም / አፕ መጠቀም ፈጽሞ አይመከርም ምክንያቱም የአንዱ ፓስወርድ ከተገኘ ሁሉም ተጋላጭ ስለሚሆን! የዲክሽነሪ ቃላትን እንደ ፓስወርድ መጠቀም አይመከርም።
ፓስወርድ ለሰዎች ማጋራት / ሼር ማድረግ ጥሩ ባይሆንም የግድ ፓስወርዳችንን ለሌሎች መስጠት ካለብን ግን ከሰጠን በኋላ መቀየር በጣም ጠቃሚ ነው።
የግል መረጃችንን እንደ ፓስወርድ ባንጠቀም በጣም ጥሩ ከመሆኑም በላይ ሀከሮች የግል መረጃችንን ለምሳሌ፡ የልደት ቀን ፣ እድሜ ፣ የጓደኞቻችንን ስም ፣ የምንወዳቸውን እንሰሳት ስም ፤ የትዳር አጋር ስም ፣ የልጆች ስም ና ሌሎችም ከኛ ጋር ትስስ ያላቸውን ነገሮች በተናጠል ወይም እንድላይ አቀናጅቶ በመሞከር ሊያጠቁን ስለሚችሉ ከዚህ እንድንጠበቅም ይረዳናል።
የይለፍ ቃል ስናዘጋጅ ፓስወርዳችን ጠንከር ያለ ግን የምናስታውሰው ሆኖ የሚከተሉትን ነገሮች ማሟላት አለበት ፡
1.) ቢያንስ ስምንት ካራክተር ና ከዚያ በላይ ርዝመት ሊኖረው ይገባል
2.) ፓስወርዳችን ካፒታል ሌተር ፣ ስሞል ሌተር ፣ ስፔሻል ካራክተርስ (ለምሳሌ፡ @ ፣ $ ፣# & ና የመሳሰሉት ማካተት አለበት)
3.) ፓስወርዳችን ለሌሎች ሰዎች ተጋልጧል ብለን ካሰብን ቶሎ መቀየር ይጠበቅብናል ፤ ባለሞያዎች የይለፍ ቃላችንን ቢበዛ በየ ሶስት ወሩ መቀየር እንዳለብን ይመክራሉ።በርግጥ ፓስወርድ በምን ያህል ጊዜ ይቀየር የሚለው ሁሉንም ላያስማማ ይችላል።
DeritaTechSolution
Facebook | Telegram | X