በሃገራችን ካሉ ቴክኖሎጂ ነክ ህጎች / አዋጆች ፤ ቢያስፈልግዎ!
 
 1. Proclamation No.1072/2018 Electronic Signature Proclamation -- አዋጅ ቁጥር 1072/2018 የኤሌክትሮኒክ ፊርማ አዋጅ 
የዚህ ህግ/አዋጅ ዋናው አላማ ለኤሌክትሮኒክ ፊርማ እውቅና መስጠት ና ይህ ፊርማ ያረፈበትን መልዐእክት የሚለዋወጡ ተሳታፊዎችን መብት ና ግዴታ መደንገግ ነው። 
2. Proclamation no. 958 Computer Crime  -- የኮምፒዩተር ወንጀል አዋጅ ቁጥር 958/2016 GC 
የኮምፒዩተር ወንጀልን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር፣ እንዲሁም ለመመርመር እንዲቻል የተዘጋጀ አዋጅ ነው።
 3. Electronic Transaction Proclamation 1205/2020 --  የኤሌክትሮኒክ ትራንዛክሽን አዋጅ ቁጥር 1205/2020 
ይህ አዋጅ የኤሌክትሮኒክ ንግድን / የኦንላይን ንግድን ወይም አገልግሎት አሰጣጥን የተመለከተ እና እነሱን ለመዳኘት የወጣ የህግ መአቀፍ ነው።
ኦንላይን ስንግዛ ስንሸጥ የተለያዮ መልዕክቶችን ኦንላይን ስንለዋወጥ ችግር ቢያጋጥም በዚህ ና በሌሎች ተያያዥ ህጎች ሊታይ ይችላል።
 4) Telecom Fraud offense Proclamation no. 761/2012 -- የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል አዋጅ ቁጥር 761/2012 G.C
ይህ አዋጅ በቴሌኮም ኢንዱስትሪው ላይ እየደረሱ ላሉና የሚደርሱ ጉዳቶችን እንዲሁም የቴሌኮም ማጭበርበን ለመከላክል ና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ነው።
5) National Payment system Proclamation/718/2011 - - የብሔራዊ የክፍያ ሥርዓት አዋጅ 718/2003
ይህ አዋጅ የብሔራዊ የክፍያ ሥርዓትን ለመደንገግ የወጣ አዋጅ ሲሆን  ፤ በ 2023 ማሻሻያ ተደርጎበት የብሔራዊ የክፍያ ሥርዓት(ማሻሻያ) አዋጅ ቁጥር 1282/2023 በሚል እንደገና ወጥቷል ።
  
