Showing posts with label Mobile network. Show all posts
Showing posts with label Mobile network. Show all posts

6G | 6th Generation Mobile Network|6ኛው ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ |



6ኛው ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ!

ስድስተኛው ትውልድ በመባል የሚጠራው አዲሱ የሞባይል ኔትዎርክ ቴክኖሎጂ ገና አገልግሎት ላይ ያልዋለ ና በሂደት ላይ ያለ ሲሆን ከ5ኛው ትውልድ (5G) ኔትዎርክ ጋር ሲነጻጸር ከ5G የበለጠ ከፍተኛ ፍጥነት እንደሚኖረው የተገመተ ሲሆን ፤ በቁጥር ለማስቀመጥ ፤ 6ኛው ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ አንድ ቴራ ባይት ዳታ/1024ጊጋ ባይት ዳታ ከአንድ ሰከንድ በታች በሆነ ጊዜ ለማስተላለፍ (ዳውንሎድ ለማድረግ) እንደሚያስችል የሚጠበቅ ሲሆን አሁን እየተጠቀምን ያለነው 5G ኔትወርክ 20GB ዳታ እስክ አንድ ሰከንድ ማስተላለፍ ወይም ዳውንሎድ ማድረግ ያስችላል።

6ኛው ትውልድ ኔትዎርክ የዳታ ፍጥነትን ለመጨመር እጅግ በጣም ከፍተኛ አቅም ያላቸው የሬድዮ ሞገዶችን የሚጠቀም ሲሆን የራሱ ኤአይ ና ማሽን ለርኒንግ ይኖረዋል ተብሏል።

መጪው 6G ኔትወርክ ለ machine to machine/M2M ግንኙነት ወይም ስማርት ዲቫይዞች እርስ በእርስ የሚያደርጉትን ግንኙነት ወይም ለInternet of Things ከ5G በበለጠ እጅጉን የተሻለ እንደሚሆን ተጠቅሷል።

6G ኔትወርክ ለስማርት ከተማ ፣ ለነጂ አልባ ተሽከርካሪዎች(Self Driving Cars) ፣ ለቨርቿል ና ኦውግመንትድ ሪያሊቲ ማርሽ ቀያሪ እንደሚሆን ና በጣም አስተማማኝ ሊያደርጋቸው እንደሚችል ከወዲሁ ተነግሮለታል። 6ኛው ትውልድ ኔትወርክ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2030 ለአገልግሎት ሊደርስ እንደሚችል ይጠበቃል።