በርካታ የአፕል ኩባንያ ምርት ና አገልግሎቶች 'i' ፊደል እንደ ስማቸው መነሻ አካተዋል ፤ ለምሳሌ ያህል ፡ iPhone , iPad , iMac , iPod ፣ iWeb , iBook , isight , iTunes , iOS ,iMovie ና የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል ፤ ለመሆኑ ምን የተለየ ትርጉም አላቸው?
የአፕል መስራች የሆነው Steve Jobs በዋና ስራ አስፍጻሚነት አፕልን ማስተዳደር ከጀመረበት ከ1997 በኋላ የመጀመሪያው ዋና ምርት እንደሆነ የሚነገርለትን iMac የተሰኘውን የወቅቱን ዘመናዊ ዴስክቶፕ
ኮምፒውተር በ1998 ሲያስተዋውቅ "i" ምን ማለት እንደሆነ ሲያብራራ ፤ "i" ከተራ ፊደልነት የዘለለ ትርጉም እንዳለው ገልፆ ፤ አፕል በምርት እና አገልግሎቶቹ ውስጥ ለመግለጽ ወይም በምርቶቹ አማካኝነት
ማስተላለፍ የሚፈልጋቸውን እሴቶች እና መርሆዎች ያመለክታል ብሎ እንደነበር ይታወሳል።
በመሆኑም በአፕል ምርቶች ላይ የምናየው የ "i" ፊደል ፤ አምስት ቁልፍ ቃላትን እንደሚወክል ይነገራል ፤ እነሱም internet , individual , instruct , inform ና inspire ናቸው።
በነኚህ ቃላት አማካኝነት አፕል ማስተላለፍ የሚፈልጋቸው መልዕክቶች ተካተዋል እነሱም empower individuals (ግለሰቦችን ማብቃት ወይም ማበረታታት), connect users to the internet
(ተጠቃሚዎችን ከበይነ መረብ ማገናኘት ), encourage learning and creativity (መማር ና ፈጠራን ማበረታታት)። instruct በሚለው ቃል አማካኝነት አፕል ተጠቃሚዎችን ለማስተማር
ያለውን ቁርጠኝነት አጉልቶ ያሳየ ሲሆን "inform" እና "inspire" የሚሉት ቃላት ኩባንያው ለደንበኞቹን እውቀትን/መረጃን መስጠት እንዲሁም መነሳሳትን ለመፍጠር ያለውን ፍላጎት ያሳያሉ።
ከዚህ በተጨማሪ አፕል "i" የሚለውን ፊደል የግል ተውላጠ ስም (Personal pronoun) ለመግለጽ ተጠቅሞበታል በመሆኑም የግላዊነትን አስፈላጊነት እና በአፕል ምርቶች ውስጥ ግላዊነትን ማላበስ አስፈላጊ
መሆናቸውን (Importance of Individuality and Personalization in Apple's Products) ለመግለጽ እንደተጠቀመበት ይነገራል።
አፕል የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሲሆን እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1976 በSteve Jobs , Steve Wozniak እና Ronald Wayne የተመሰረተ መሆኑ ይነገራል። ካምፓኒው ከተመሰረተ በኋላ
የመጀመሪያው ስራ አስፈጻሚ Michael Scott የነበረ ሲሆን ይህ ግለሰብ በወቅቱ የመስራቾቹ አጋር በነበረው ሚሊየነር Mike Markkula የተቀጠረ እንደነበረ ይነገራል ፤ ከዚያም Steve Jobsን
ጨምሮ ሎሎች ስራ አስፈጻሚዎች አፕልን ሲመሩ እንደነበር ይታወሳል።
Steve Jobs በ1997 CEO በመሆን ኩባንያው በወቅቱ ደርሶበት ከነበረው ቀውስ እንዲያንሰራራ በማድረግ አዳዲስ ምርት ና አገልግሎቶችን በማስተዋወቅ ህይቱ እስካለፈበት እስከ 2011 ድረስ አፕል ትርፋማ ና
ተወዳጅ እንዲሆን አስችሏል። በአሁኑ ወቅት Tim Cook እየመራው ይገኛል ፤ Cook አፕልን በስራ አስፈጻሚነት ሲመራ ይህ የመጀመርያው እንዳልሆነ ይነገርለታል ፤ ከዚህ ቀደም በ2004 ፣ በ2009 ና በ
January 2011 Steve Jobs ለህክምና ፍቃድ በወጣባቸው ጊዚያት ለወራት Jobsን በመተካት CEO ሆኖ እንደነበር አይዘነጋም።
Showing posts with label iPad. Show all posts
Showing posts with label iPad. Show all posts
Meaning of "i" in Apple Products | history of Apple | Steve Jobs | Apple Products |Apple|iPod|iPad|iPhone|
በApple ምርቶች ላይ የምንመለከተው "i" ምን ትርጉም አለው?
Subscribe to:
Posts (Atom)