Showing posts with label websites. Show all posts
Showing posts with label websites. Show all posts

best websites we must visit | Must know websites |

ለተለያዪ ጉዳዮች የሚጠቅሙን ምርጥ ድረገጾች ፤ ይሞክሯቸው ፡


1. photopea.com
ኮምፒውተራችን ወይም ስልካችን ላይ ምንም አይነት ሶፍትዌር መጫን ሳይጠበቅብን የፎቶ ኢዲቲንግ ና ግራፊክ ዲዛይን ስራ መስራት ያስችለናል ።
2. remove.bg
ከፎቷችን ጀርባ ያለ ማንኛውንም ምስል ለማስወገድ ወይም በፈለግነው ምስል ውይም ከለር ለመቀየር በሰከንድ የሚያስችለን ድረገጽ ነው።
3. circlecropimage.com
ለተለያዩ ጉዳዮች ፎቶ በክብ ቅርጽ መቁረጥ ቢያስፈልገን ፤ በቀላሉ በምንፈልገው መልኩ circle ይቆርጥልናል።
4. storyset.com
ለማስተማሪያነት ወይም የተለያዩ ነገሮችን ለማስረዳት የሚረዱንን ምስሎች ሰርች በማድረግ በምንፈልገው መልኩ አስተካክለን ወይም Customize አድርገን ዳውንሎድ ማድረግ ያስችለናል።ከዚህ በተጨማሪ

የመረጥነውን ምስል customize አድርገን በgif ወይም በቪዲዮ ፎርማትም ዳውንሎድ ማድረግ እንችላለን።
5. pdf24.org
ይህ በጣም የተደራጀ የፒዲኤፍ / pdf solution ነው።
pdf ፋይሎችን edit ማድረግ ፣ መነጠል ፣ የተለያዩ pdf ፋይሎችን ማዋሃድ ፣ pdfን ወደ image ወይም image ወደ pdf መቀየር ፣ pdf ፋይሎችን sign ማድረግ እና የመሳሰሉትን ነገሮች
ምንም አይነት pdf ሶፍትዌር መጫን ሳያስፈልገን ማከናወን ያስችለናል።
6. Quillbot.com
የተለያዩ የእንግሊዝኛ ጽሁፎችን የምናዘጋጅ ከሆነ ፤ የሰዋሰው ፣ የአገላለጽ ና ሌሎችም ችግሮች እንዳያጋጥሙን በሚገባ እርማት ይሰጠናል።
7. diffchecker.com
በተለያዩ ዶክመንቶች ለምሳሌ ፡ በወርድ ፣ በኤክሴል ፣ በቴክስት ዶክመንቶች እንዲሁም በምስሎች መካከል ያለውን ልዩነት ያሳየናል። ዶክመንቱን አፕሎድ በማድረግ ወይም ቴክስቱን ብቻ ፔስት በማድረግ
ልንጠቀምበት እንችላለን።
8. 10minutemail.com
ለተለያዩ ጉዳዮች ጊዜያዊ የኢሜይል አድራሻ ቢያስፈልገን የ10ደቂቃ የኢሜይል አድራሻ ይሰጠናል ፣ ጊዜውን እንደ አስፈላጊነቱ ተጨማሪ ደቂቃዎችን በመጠየቅ ማራዝም እንችላለን።
9. alternativeto.com
ለፈለግነው የስልክ ወይም የኮምፒውተር መተግበሪያ አማራጮችን ከነማብራሪያው ይሰጠናል። ለምሳሌ፡ አንድ በጣም የወደዳችሁት መተግበሪያ ክፍያ ቢጠይቃችሁ ና መክፈል ባትችሉ ፤ ከሱ ጋር ተመሳሳይ አገልግሎት
የሚሰጡ አማራጭ መተግበሪያዎችን ፈልጎ ሊያሳየን ይችላል።

እነዚህን ድረገጾች ካላወቁ ወደ ኋላ ቀርተዋል!|Powerful Websites we need to know|Useful websites

በዚህ የቴክኖሎጂ ዘመን ነገሮችን ለማከናወን በጭራሽ መድከም የለብዎትም በቀላሉ ፤ ጊዜን ፣ ገንዘብን እንዲሁም ድካምን መቀነስ የሚችሉባቸው ሁሌም ስራዎን እጅጉን የሚያቀሉ ድረገጾችን ካሉበት አፈላልገን ፣ ፈትሸን በተግባር አቀረብንልዎ ፤ ይሞክሯቸው!