የያዝነው የፈረንጀቹ ጥቅምት ወር/October የCyberSecurity ግንዛቤ መፍጠርያ ወር ነው !
ለመሆኑ ሳይበር ደህንነት/CyberSecurity ምንድነው? አረ ሳይበር / Cyber ብሎ ነገረስ ምንድ ነው?
Cyber / ሳይበር የሚለው ቃል በግርድፉ ሲተረጎም ከኮምፒውተር ወይም ከኮምውተር ኔትወርክ በተለይ ከ ኢንተርኔት ጋር ተዛማጅነት ያለው ወይም ኮምፒውተር ና የኮምፒውተር ኔትዎርክን እንዲሁም ሌሎች የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ውጤቶችን የሚያካትት ማለት ሲሆን ፤ CyberSecurity ማለት ደግሞ ግለሰብን ፣ ድርጅትን ወይም ሃገርን ና መረጃዎቻቸውን ቴክኖሎጂን መሰረት አድርገው ከሚፈጸሙ ጥቃቶች መከላከል ወይም መጠበቅ ነው።
CyberSecurity የሚለው ቃል የተለያዩ ቦታዎች ላይ አንደ አንድ ቃል አንዳንዴም እንደ ሁለት ቃላት (Cyber Security) ተደርጎ ሲጻፍ ይስተዋላል ፤ ነገር ግን እንደ ኢንዱስትሪው ስታንዳርድ ና ትክክሀኛው አጻጻፍ አንድ ቃል ነው ይባላል።