ስታርሊንክ የአሜሪካ ኤሮስፔስ ኩባንያ በሆነው የኤሎን ማስክ ስፔስኤክስ / spacex ባለቤትነት የሚተዳደር የሳተላይት ኔትወርክ/ ኢንተርኔት አገልግሎት ሲሆን ዋናው ዓላማው በዓለም ዙሪያ ላሉ የኢንተርኔት አገልግሎት ለማያገኙ ገጠራማና ሩቅ የአለም ክፍሎች ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የኢንተርኔት አገልግሎት በዝቅተኛ ዋጋ እንዲያገኙ ማድረግ ነው። ብዙ ቁጥር ያላቸውን LEO ወይም Low Earth Orbit / ለመሬት በጣም ቅርብ የሆኑ ሳተላይቶችን በጋራ በማሰማራት የፋይበር ኦፕቲክና የሞባይል ኔትዎርክ ግንኙነት የማያገኙ አካባቢዎችን አስተማማኝና ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ያደርጋል። የስታርሊንክ የሳተላይት ኢንተርኔት ለOnline Gaming, ለVideo Conferencing,ለVideo call ና ለሌሎች real-time ስራዎችን በፍጥነት መከወን እንድንችል የሚረዳ ፈጣን የሳተላይት broadband ኢንተርኔት አገልግሎት ነው። StarLinkን ለመጠቀም በጣም ቀላል የሆነ ና ከቦታ ቦታ ማንቀሳቀስ የምንችለው satelite Dish ያለው ሲሆን ማንኛውም ቦታ ላይ በማስቀመጥ እራሱን ከሳተላይት ጋር ማስተካከል ይችላል። በአሁኑ ሰአት በተወሰኑ የአለማችን ሃገራት ስራ የጀመረው StarLink በአፍሪካም የተለያዩ ሃገራት ላይ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ለምሳሌ: ናይጀርያ፣ ማላዊ፣ ዛምብያ፣ ሩዋንዳ፣ ኬንያ፣ቤኒን፣ኢስትዋና ሞዛምቢክ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሲሆኑ በቅርቡም ወደ ሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ላይ የሚጀምር ይሆናል።
No comments:
Post a Comment