Facebook fined by DPC | TechNews | Tech News| Facebook| Meta |ፌስቡክ | ፌስቡክ ቅጣት ተጣለበት


የፌስቡክ ፓረንት ካምፓኒ Meta የ91ሚሊዮን ዮሮ ቅጣት ተጣለበት!



🖌 ባሳለፍነው አርብ መስከረም 27, 2024 የአየርላንዱ የውሂብ ጥበቃ ኮሚሽን / Data Protection Commission/DPC እንዳስታወቀው በ2019 አጋጥሞ የነበረውን የፌስቡክ ደንበኞች መረጃ ጥሰት ላይ ሲያካሂድ የነበረውን አመታትን የፈጅ ምርመራ ሲያጠናቅቅ በፌስቡክ ና ኢስታግራም ተጠቃሚዎች የይለፍ ቃላቻውን ያለምንም ምስጠራ ወይም ኢንክሪፕሽን በግላጭ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2012 ጀምሮ ሲያስቀምጥ እንደነብር ና በዚህም ምክንያት እስከ 20,000 የሚሆኑ ሰራኞች የተጠቃሚዎችን የይለፍ ቃል ያለአግባብ ሲመለከቱ እንደነበር አስረድቷል።

🖌 ሜታ የደንበኞቹን መረጃ ደረጃውን ባልጠበቀ መልኩ ና የGDPR/General Data Protection Regulationንን ህግ ባልተከተለ መልኩ በማስቀመጡ ና ክስተቱንም በጊዜ ለሚመለከተው አካል በ72 ሰዓታት ውስጥ ባለማሳወቁ የ$101.5M ዶላር ወይም የ91M ዮሮ ቅጣት እንደተጣለበት አስታውቋል።

🖌እንደ DPC ገለጻ ይህ ሁነት የደንበኞች መረጃ ስጋት ላይ ጥሎ የነበረ ቢሆንም የይለፍ ቃሎቹ ለውጪ አካላት አልተሰጡም ብሏል።ሜታም በጊዜው ችግሩን አምኖ እንደነበረ ይሚታወስነው።

https://Youtube.com/DeritaTechSolution Facebook : https://Facebook.com/DeritaTech Telegram: https://t.me/DeritaTech

Google Search Tips | ጉልግ | How to Search on Google-Amharic |ጉግል መፈለጊያ | Google


Google Search Tips !


🎯 Use quotation marks (" ") for exact word

Google ላይ የሆነ ነገር እየፈለጉ ከሆነ ነገር ግን በማይዛመዱ ውጤቶች ከተጨናነቁ፣ ጥያቄዎን በጥቅስ ምልክት ውስጥ ያድርጉት። Google በጥቅሶች ውስጥ ከፃፉት ጋር በትክክል የሚዛመዱ ውጤቶችን ብቻ ያሳይዎታል። ለምሳሌ፡ "DeritaTech" የሚል ቢሰጡት እሱን ብቻ የተመለከተ መረጃ ብቻ ያገኛሉ።

🎯 Use hyphen / Minus sign to exclude words is a research result

ጉግል ላይ መረጃ ሲፈልጉ ማስቀረት የሚፈልጓቸው ቃላት ወይም የፍለጋ ውጤቶች ካሉ የመቀነስ ምልክትን በመጠቀም እንዲቀር የሚፈልጉትን ቃል ይጻፉ ልምሳሌ፡ Apple ይሚል ጎግል ላይ ቢፈልጉ የፍለጋ ዉጤቱ ስለ አፕል ካምፓኒ ና ስለ አፕል ፍሩት እንዲሁም ሌሎች አፕል የሚል ስያሜ ያላቸውንም ነገሮች ሊያካትት ይችላል ፤ የፍለጋ ውጤቱ fruit ወይም foodን ሳያካትት አፕል ካምፓኒን የተመለከቱ መረጃዎች እንዲሰጠን apple -food -fruit አድርገን መፈለግ እንችላለን። ይህ የሚሰራው ከአንድ በላይ ትርጉም ላላቸው ቃላት ብቻ ነው።

🎯 Use site to limit search to a specific site

ከሆነ ዌብሳይት መረጃ የምንፈልግ ከሆነ ና እንዳጋጣሚ ያዌብሳይት ሰርች ማድረጊያ ከሌለው ፤ ጉግል ላይ site: አድርገን የዌብሳዩን ስም ና ከዚያ ሳይት ላይ የምንፈልገውን ቃል እናስገባለን ። ለምሳሌ፡ site:deritatech.blogspot.com passport የሚል ብንጽፍ ከዚህ ዌብሳይት ላይ ብቻ ፓስፖርት የሚል ቃል ያለበትን መረጃ ያመጣልናል።

🎯 Limit Google Search to Specific Domain

ጉግል ላይ መረጃ ስንፈልግ እኛ ከምንፈልጋቸው ዶሜኖች ብቻ ፈልጎ እንዲያመጣልን ማድረግ እንችላለን ፤ ለምሳሌ፡ healthcare የሚል ቃል የምንፈልግ ከሆነ ና የዚህ ፍለጋ ውጤት ከ .org ዶሜን ላይ ብቻ እንዲመጣ ከፈለግን site:org healthcare ብለን ጉግል ሰርች ላይ እንጽፋለን ለሌሎች ዶሜኖችም እንደዛው ማድረግ ይቻላል ፤ ትምህርታዊ መረጃ ብትፈልጉ ከ Academic institutions ብቻ ፈልጎ እንዲያመጣላችሁ ፤ site:edu healthcare ማድረግ ይቻላል።

🎯 Easily Search for related or Similar websites

ጉግለ ላይ እርስዎ ከሚያውቁት ድረገጽ ወይም ዌብሳይት ጋር ተቀራራቢ የሆነ ወይም መሰል አገልግሎት የሚሰጠውን ወይም አማራጭ የሚሆኑትን ማወቅ ቢፈልጉ ፤ በ ጉግል መፈለጊያ ሳጥን ላይ Related የሚል ቃል በማስቀደም የዌብሳይቱን ስም ይጻፉ። ለምሳሌ፡ Related: amazon.com ብንል የአማዞን አማራጭችን ሁሉ ይዘረዝርልናል።

🎯 Perform Advanced Search

ጉግል ላይ የላቀ ፍለጋ ወይም አድቫንስድ ሰርች ማድረግ ከፈለጉ ፤ google.com ላይ በቀኝ በኩል ከታች settings/ቅንብሮች የሚል ያገኛሉ አለሱን ስንጫነው Advanced Search ና ሌሎችም አማራጮችን እናገኛልን እንጠቀምባቸው።

ስልክ ስንገዛ ማየት ያለብን ዋና ዋና ነገሮች! | Smartphone Buying Guide | How to Buy Smartphones-Amharic


ስልክ ስንገዛ ማየት ያለብን ዋና ዋና ነገሮች!

አዲስም ይሁን ያገለገለ ስልክ በተለይ እስማርት ስልክ ስንገዛ አቅማችንን ባገናዘበ መልኩ የሚከተሉትን ነገሮች ከግምት አስገብተን ብንገዛ ስልካችን በተሻለ መልኩ ሊጠቅመን ይችላል! ስልክ ለመግዛት ስናስብ መጀመሪያ የያዘነውን በጀት ባገናዘበ መልኩ የስልኩን Specification / ስልኩ ምን ምን ነገሮች እንዳሉት ወይም ምን ምን ገጽታዎች እንዳሉት ማየት አስፈላጊ ነው ፤ የስልኩ ስፔሲፊኬሽን ላይ ሁሌም ከማይጠፉ ና እኛም ሁሌ ማየት ያለብንን ነገሮች የተወሰኑትን እን መልከት፤


📷

ካሜራ


አሁን ላይ ስልክ ስንገዛ አብዛኞቻችን ቅድምያ የምናየው ና ማየትም ያለብን ካሜራውን ነው ፤ ምክንያቱም ስማርት ስልክ መጠቀም ከጀመርን ወዲህ ሌላ ተጨማሪ ካሜራ መያዝ ትተናል ስለዚህ ስልካችን ጥሩ ካሜራ ካለው ለትውስታም ይሁን ለማስረጃ ማስቀረት የፈለግነውን ነገር ማንሳት እንድንችል አቅምን ባገናዘበ መልኩ ጥሩ ካሜራ ያስፈልገናል፤ የአንድ ስልክ የካሜራው ጥራት ለማወቅ በርካታ ነገሮች ቢታዮም በዋናነት ግን የስልኩ ካሜራ MegaPixel / MP መታየት አለበት ፤ ይህ በካሜራው የሚነሳውን ፎቶ ጥራት የሚወስን ነው ፤ ከፍያለ ሜጋ ፒክስል ያለው ካሜራ ወይም ስልክ የተሻለ ጥራት ያለው ፎቶ ያነሳል።


💾

Internal Storage


ይህ ስልካችን ሚሞሪ ካርድ ሳንጠቀም ፤ ምን ያህል ዳታ እንደሚይዝልን የሚወስን ነው ፤ ስልካችን ሚሞሪ ካርድ ስሎት ከሌለው ይህ ከፍ ያለ ቢሆን ይመከራል ፤ ስልካችን ሚሞሪ የሚጠቀም ከሆነ የግል መረጃችንን ወደ ሚሞሪው መውሰድ ስለ ምንችል ብዙም አሳሳቢ አይሆንም ፤ ነገር ግን ሁሌም ከፍ ያለ GB Internal Storage ቢኖረው አይከፋም።
🖌

RAM / Random Access Memory

/ ራም
ራም ለስልካችን በጣም ወሳኝ አካል ሲሆን ፤ ስልካችን ፈጣን እንዲሆን የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል ፤ ስልካችን ላይ በተለይ ጌም የምንጫወት ከሆነ ፤ ቪዲዮ ኤዲቲንግ የምን ሰራ እና ሌሎች ጠንከር ያሉ ስራዎችን የምሰራ ከሆነ ስልካችን ከፍ ያለ GB ራም ያስፈልገዋል ፤ ስለዚህ ለስካችን ከፍ ያለ GB RAM እንምረጥ ።
🟢

Processor / CPU


ፕሮሰሰር ወይም ሲፒዩ ለስካችን ልክ እንደ አንጎል ነው ፤ ማንኛውም ስልካችን የሚያከናውነው ነገር በፕሮሰሰር ትዕዛዝ የሚፈጽም ነው ፤ የፕሮሰሰር ፍጥነት በጊጋ ኸርዝ ፐር ሰከንድ/GHz/s የሚለካ ሲሆን ይሄም ኮምፒውተራችን በሰከንድ ምን ያህል ቢሊየን ትዕዛዞችን እንደሚያከናውን ይገልጻል ፤ ከፍ ያለ GHz/s ፕሮሰሰር ፍጥነት ያለውን ስልክ መምረጥ ጥሩ ነው።
🖥

Display / Screen Size ና Resolution/ጥራት


ስልኮች በተለያየ የስክሪን መጠን ና የስክሪን ሪዞሉሽን ሊመጡ ይችላሉ ፤ የስክሪን ሳይዝ እንደየፍላጎታችን የሚወሰን ሲሆን በጣም ካነሰ ለአንዳንድ ስራዎች ላይመቸን ይችላል ለምሳሌ ለማንበብያ ፤ ፎቶ ፣ ቪዲዮ ኤዲት ለማድረግ እና ለመሳሰሉት ነገሮች ከፍ ያለ ቢሆን ጥሩ ነው ፤ ነገር ግን ለአያያዝም መመቸት ስላለበት ለሁሉም ተስማሚ / ideal SCreen size ብንመርጥ ይመከራል ፤ ከ 5.5 እስከ 6 ኢንች ስክሪን ለብዙዎቻን ተስማሚ ነው ፤ የስክሪን ሪዞሉሽን ደግሞ HD , Full HD ወይም QHD/Quad High Definition (QHD) ቢሆን መልካም ነው።
🔦

Battery Life / የስልካችን የባትሪ ቆይታ


ስልካችንን እንደልብ እንድንጠቀምበት ባትሪው አስተማማኝ መሆን አለበት ፤ አዲስም ይሁን ያገለገለ ስልክ ስንገዛ Battery Capacity ማየት ይገባናል ፤ የባትሪ ካፓሲቲ በሚሊ አምፕ አወር / mAH የሚለካ ሲሆን ከፍ ያለ mAH ያለው የስልክ ባትሪ የተሻለ ቆይታ ይኖረዋል ፤ ለምሳሌ፡ ከ2000mAH ፤ 3000mAH ወይም ከዚያ በላይ ያለውን መምረጥ አለብን።
🔒

ስልኩ ያለው የደህንነት መጠበቂያ መንገዶች / Security Features


አሁን ላይ በርካታ ስልኮች ከፓተርን ና ከይለፍ ቃል ባለፈ ተጨማሪ የደህንነት ማስጠበቂያ መንገዶች አሏቸው ለምሳሌ ፡ ፊንገር ፕሪንት ሴንሰር / Finger Print Sensor ፣ የአይሪስ ሴንሰር ስካነር / Iris scanner/የአይን ብሌን ሰካነር አሏቸው ፤ finger print sensor ና iris scanner ስልካችንን እኛ ብቻ አንሎ ማድረግ እንድንችል አንዲሁም አንዳንድ ክፍያዎችን ለመክፈል እንደ ማረጋገጫ ልንጠቀምባቸው እንችላለን። ይህ ፊቸር ያላቸው ስልኮች ከሌሎቹ ስልኮች የተሻለ ደህንነት ለስልካችን ይሰጣሉ ፤ ስለዚህ ከሌለው ስልክ ያለውን መምረጥ የተሻለ ነው።
🖌

Android / IOS version / የስልካችን ስረአተክወና ወይም ኦፕሬቲንግ ሲስተም


ስልካችን ህይወት ኖሮት መጠቀም እንድንችል ፤ ከስልካችን ጋር እንደልብ መነጋገር እንድንችል ፤ ስልካችን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ያስፈልገዋል ፤ አብዛኞቹ ስልኮች Android ወይም IOS የተጫነባቸው ሲሆኑ ፤ የቅርብ ግዜ የሆኑትን አንድሮይድ ወይም አይ ኦ ኤስ መምረጥ ስልካችን ብዙ አዳዲስ ፊቸሮች እንዲኖሩት እንዲሁም ደህንንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ይረዳል።
📌

ስልኩ የተሰራበት ማቴሪያል


ስልኮቻችን ከተለያየ ነገር ሊሰሩ ይችላሉ ፤ በተለይ የውጪው ከቨር ከፕላስቲክ ፣ ከመስታወት እንዲሁም ብረትም ይኖራል ፤ ስለዚህ ስልካችን ወድቆ ሳይከፋው እንዲነሳ የተሻለውን መምረጥ ይገባል ፤ ፕላስቲክ ና ብረት ከሆነ ቢወድቅ ከተወሰነ ከፍታ ድረስ የመቁቁም አቅም አላቸው ፤ መስታወት ነክ ከሆነ አለቀለት ። የስልካችን ውጫዊ አካል ከምን እንደተሰራ ለማወቅ በስልኩ ሞዴል ኦንላይን ብንፈልግ እናገኛለን።
☎️

ስልኩ የሚሰራበት የኔትወርክ አይነት


በ1979 በጃፓን ከተዋወቀው ና ድምጽ / voice call ብቻ ከሚሰራው ከመጀመሪያው ትውልድ/1G ኔትወርክ ጀምረን 2G , 3G , 4G , 5G እያልን አሁን ላይ ስድስተኛው ትውልድ / 6G ሙከራ ላይ ይገኛል። ስለዚህ ከዘመኑ ጋር አብረን ለመጓዝ የምንገዛው ስልክ አሁን ላይ ቢያንስ 4G የሚሰራ ቢሆን በጣም ጥሩ ነው።
መልካም ንባብ!

የNeuraLink ብላይንድሳይት ፈቃድ አገኘ|NeuraLink's Blindsight has got FDA's Approval


የኤሎን መሰክ ኩባንያ የሆነው NeuraLink ማየት የተሳናቸውን እንዲያዩ ለማደረግ የሚያስችል ና በጭንቅላት ውስጥ የሚቀበረው Blidsight የተሰኘው በሙከራላይ ያለው ኤሊክትሮኑክስ ቺፕ የ FDA(የአሜሪካ ምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ባለ ስልጣንን) ፍቃድ ማግኘቱን አስታወቀ!
ይህንን ኤሊክትሮኑክስ ቺፕ ያስገጠሙ ማየት የተሳናቸው ሰዎች ከውልደት ጀምሮ የማየት ችግር ቢኖርባቸውም ማየት እንዲችሉ ያደርጋልም ተብሏል።
የኩባንያው ባለቤት የሆነው Elon musk በ X ገፁ ባሰፈረው መረጃ ይህ በሙከራ ላይ ያለው blindsight የተባለው ዲቫይዝ በአንጎላችን ውስጥ የሚገኘው ቪዥዋል ኮርቴክስ የተባለው ና በዋነኛነት ከዓይኖች የተቀበለውን ምስላዊ መረጃዎች የመተርጎም እና የማቀናበር ሃላፊነት ያለበት ክፍል እስካልተጎዳ ድረስ ከልጅነት ጀምሮ ማየት የተሳነው ሁሉ እይታው እንዲመለስለት ያደርጋል ሲል መግለፁን India Today ዘግቧል።
Elon musk አክሎም በዚህ መንገድ የሚመለስ እይታ መጀመሪያ ላይ ዝቅተኛ ቢሆነም ውሎ ሲያድር ከተፈጥሮ እይታ የተሻለ እንደሚሆንም ተስፋ ሰጥቷል።
በተያያዘ መረጃ ኒውራሊንክ የQuadriplegia (Tetraplegia) ማለትም በህመም ምክንያት እጅና ና እግራቸው አልታዘዝ ያላቸው ፤ በሙከራ ላይ ላለው በጭንቅላት ውስጥ ተቀብሮ ስልክ ና ኮምፒውተርን ማዘዝ ለሚያስችለው ኤሊክትሮኑክስ ቺፕ ትግበራ ተሳታፊ መሆን ለሚፈልጉ ምዝገባ ላይ መሆኑን NeuraLink.com አስታውቋል።
ወይ ቴክኖሎጂ አያስብልም ታድያ!
መልካም ንባብ!
DeritaTechSolution
Facebook
Telegram
X

Barcode|Difference Between Barcode and QR Code-Amharic|QR Codes|How to Create QR Codes

ስለ QR code ና Barcode ምንያህል ያውቃሉ?

Quick-Response Code/QR Code በመባል የሚታወቀው በማሽን የሚነበብና በውስጡ የተለያዩ መረጃዎችን ምስላዊ በሆነ መልኩ የሚይዝልን ሲሆን በማሽን ሲነበብ በሁሉም አቅጣጫ መነበብ የሚችል ነው።
Barcode ልክ እንደ QR code መረጃዎችን የሚይዝ ሲሆን : ከQR code ጋር ሲነፃፀር መጠነኛ የመረጃ አይነቶችን ወይም መጠነኛ መረጃ(እስከ 100 character) ብቻ የሚይዝ ሲሆን QR code እስከ 2500 character /ፊደላትን ሊይዝልን ይችላል። ባርኮድ በOne Dimensional Code ና Two Dimensional Code ያለ ሲሆን በብዛት የሚታወቀው የባርኮድ አይነት One Dimensional Code ነው ። ይህ የባርኮድ አይነት የተለያዩ ምርቶች ላይ የምናየው ሲሆን ቁልቁል የተደረደሩ ና የተለያየ ውፍረት ያላቸው መስመሮችን የ ያዘና በማሽን ሲነበብም ከላይ ወደታች ብቻ ነው።
Barcode በአብዛኛው የማይዝልን መረጃ የተለያዩ ምርቶችን አይት : ዋጋ :የተመረተበትን ዘመን ና ሌሎች መሠል መረጃዎችን ነው። እነዚህ መረጃዎች በባርኮድ ሪደር ሲነበቡ በቀጥታ ወደ ሲስተም እንዲገቡ ይደረጋል። Two Dimensional barcode ማትሪክስ ኮድ ወይም Micropattern code በመባል ይጠራል።
ከTwo dimensional Barcode አይነቶች አንዱ QR Code ሲሆን ሁሉም 2D brcodes ግን QRcode ላይሆኑ ይችላሉ።
QR code በውስጡ በጣም ብዙ መረጃዎችን ሊይዝልን ይችላል ለምሳሌ: የተለያዩ ሊንኮች , text, email, sms, wi-fi network information , Download link, social media information ለምሳሌ:የፌስቡክ :የትዊተር :ቴሌግራም ና የመሳሰሉትን የሶሻል ሚዲያ አካውንቶቻችንን ሼር ልናደርግበት እንችላለን ፤ ሌሎች መረጃዎችን መያዝ ይችላል።
QR code ጉዳትን/damageን በቀላሉ የሚቋቋም ሲሆን ፕሪንት ከተደረገ በኋላ ቢተሻሽ ፣በመጠኑ ቢቀደድ የያዘው መረጃ በቀላሉ አይጎዳም: Barcode ግን በአንጻሩ ከተሻሸ በቀላሉ መረጃው ሊጠፍ ወይም ላይነበብ ይችላል።
QR code እና Barcodeን ለማንበብ በስልካችን ላይ ማንበቢያው ሊኖረን ይገባል ፤ አንዳንድ ስልኮች የራሳቸው built-in scanner ሲኖራቸው አንዳንድ ስልኮች ላይ ደግሞ scan ለማድረግ የግድ scanner application download አድርገን መጫን ይጠበቅብናል።
ባርኮድ በ1951 ኖርማን ጆሴፍ ና በርናንድ ሲልቨር የተፈጠረ ሲሆን QR Code ደግሞ በ1994 ዴንሶ ዌቭ በተባለ የጃፓን አውቶሞቲቭ ኩባንያ የተፈጠረ ነው።
ባርኮዶ ና QR code አኛም ለፈለግነው አላማ አዘጋጅተን መጠቀም እንችላለን፤ ለማዘጋጀት ኦንላይን የተለያዩ ዌብሳይቶች አሉ እንዲሁም የተለያዩ አፓችን ዳውንሎድ አድርገን ማዘጋጀትም እንችላለን ፤ ለምሳሌ: https:qr-code-generator.com ላይ , በአፕ ደሞ QR and Barcode scanner የሚባለውን አውርደን ማዘጋጀት ይቻላል።
QR codeን በተለያየ ቀለም ና ዲዛይን ማዘጋጀት ይቻላል ፤ አንዴ ካዘጋጀንም በኋላ ማስተካከል ወይም Customize ማድረግ ይቻላል።
ይህ መረጃ ጠቃሚ ሆኖ ካገኛችሁት ለሌሎችም እንዲደርሳቸው ያድርጉ!

DeritaTechSolution
Facebook
Telegram
X

Clipboard AI|Ui path|Copy paste automation|Don't copy and paste before watching this

ስለ ክሊፕ ቦርድ ኤአይ / Click board AI መረጃ አለዎት?

Clip board AI Uipath በተሰኘ የሶፍትዌር ካምፓኒ አበልፃጊነት ለአገልግሎት የዋለ ና ተለምዷዊውን የኮፒ ፔስት ስራ እጅጉን ያዘመነ እንዲሁም ጊዜን በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀንሰ የኮምፒውተር መተግበሪያ ነው። ክሊፕ ቦርድ ኤአይ አርተፊሻል ኢተለጀንስን በመጠቀም ከምን አይነት ሰነድ ላይ ምን ና የት ኮፒ ማድረግ እንደፈለግን በመረዳት ነገሮችን በጣም ቀለል አድርጎልናል ፤ ክሊፕ ቦርድ ኤአይን በመጠቀም የካሽ ሬጂስተር ወረቀትን ጨምሮ ከማንኛውም አይነት ደረሰኞች ፣ እስካን ከተደረጉ ወረቀቶች ፣ መታወቂያዎች ፣ ከፓስፖርት እና ከሌላ ከማንኛውም ስካን ከተደረገ ሰነድ ቴክስቶችን ወይም ፅሁፎችን በመነጠል መውሰድ ብቻ ሳይሆን ፎርማቱ እንደተጠበቀ በፈለግነው ቦታ ለምሳሌ ፡ ወርድ ላይ ፣ ኤክሴል ላይ ፣ የተለያዪ ፎርሞች ላይ ፔስት ማደረግ እንችላለን ፤ ክሊፕ ቦርድ ኤአይ በጣም ብዙ ጥቅሞች ያሉት ሲሆን ለአጠቃቀም በጣም ቀላል የሆነ በጣም ትንሽ ሳይዝ ያለው መተግበሪ ነው። ክሊፕ ቦርድ ኤአይን መጠቀም ከፈለጉ ይህን ማስፈንጠሪያ በመጫን ያገኙታል ፡https://www.uipath.com/product/clipboard-ai

what is Starlink?Starlink|Satelite Internet|SpaceX|Elon Musk|ስታርሊንክ

🌎 Starlink ምንድን ነው?🌍

ስታርሊንክ የአሜሪካ ኤሮስፔስ ኩባንያ በሆነው የኤሎን ማስክ ስፔስኤክስ / spacex ባለቤትነት የሚተዳደር የሳተላይት ኔትወርክ/ ኢንተርኔት አገልግሎት ሲሆን ዋናው ዓላማው በዓለም ዙሪያ ላሉ የኢንተርኔት አገልግሎት ለማያገኙ ገጠራማና ሩቅ የአለም ክፍሎች ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የኢንተርኔት አገልግሎት በዝቅተኛ ዋጋ እንዲያገኙ ማድረግ ነው። ብዙ ቁጥር ያላቸውን LEO ወይም Low Earth Orbit / ለመሬት በጣም ቅርብ የሆኑ ሳተላይቶችን በጋራ በማሰማራት የፋይበር ኦፕቲክና የሞባይል ኔትዎርክ ግንኙነት የማያገኙ አካባቢዎችን አስተማማኝና ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ያደርጋል። የስታርሊንክ የሳተላይት ኢንተርኔት ለOnline Gaming, ለVideo Conferencing,ለVideo call ና ለሌሎች real-time ስራዎችን በፍጥነት መከወን እንድንችል የሚረዳ ፈጣን የሳተላይት broadband ኢንተርኔት አገልግሎት ነው። StarLinkን ለመጠቀም በጣም ቀላል የሆነ ና ከቦታ ቦታ ማንቀሳቀስ የምንችለው satelite Dish ያለው ሲሆን ማንኛውም ቦታ ላይ በማስቀመጥ እራሱን ከሳተላይት ጋር ማስተካከል ይችላል። በአሁኑ ሰአት በተወሰኑ የአለማችን ሃገራት ስራ የጀመረው StarLink በአፍሪካም የተለያዩ ሃገራት ላይ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ለምሳሌ: ናይጀርያ፣ ማላዊ፣ ዛምብያ፣ ሩዋንዳ፣ ኬንያ፣ቤኒን፣ኢስትዋና ሞዛምቢክ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሲሆኑ በቅርቡም ወደ ሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ላይ የሚጀምር ይሆናል።