known Smartphone Operating systems|Mobile Operating System Types | Smartphone |የስልክ ስረአተክወናዎች

የስልክ ኦፕሬቲንግ ሲስተም / ስረአተ ክወና አይነቶች



የስልካችን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከስልካችን ጋር እንደልብ መነጋገር እንድንችል ፣ የፈለግነውን አፕሊኬሽን መጫን ና መጠቀም እንድንችል ፣ የስልካችን ሃርድ ዌር ህይወት ዘርቶ መጠቀም እንድንችል ፣ እንደ አስፈላጊነቱ ሚሞሪ መመደብ / Memory allocation and deallocation ፣ ፕሮሰስር ለሚያስፈልጋቸው ፕሮሰሶች መመደብ እና ሌሎችም በርካታ ጥቅሞች አሉት ። ዋና ዋና የስልክ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞችን ስንመለከት ፤

1. Android

ይህ አሁን ላይ በርካታ ስማርት ስልኮች ላይ ተጭኖ የሚመጣ የኦፕሬቲንግ ሲስተም አይነት ሲሆን በጉግል ካምፓኒ የበለጽገም ነው። Android ለእያንዳንዱ አዳዲስ ቨርዥን የተለያየ ስያሜ በመስጠት ይታወቃል። ለምሳሌ ፡ Cupcake(Version 1.5), Donut(version 1.6), Eclair (version 2.0 - 2.1), Oreo(Android version 8.0-8.1), Kitkat (version 4.4) , Vanila Ice cream(Android Version 15) etc.

2. iOS

ይህ Operating system በአፕል ስልኮች ና ሌሎች የአፕል ምርቶች ላይ ለምሳሌ በiPhone , iPad Tablet... ላይ የሚሰራ ነው ፤ ከአንድሮይድ ቀጥሎ የታወቀ ስረአተ ክወና ሲሆን ጠንከር ባለ የደህንነት ፊቸርም ይታወቃል።

3. Blackberry OS

ይህ ኦፕሬቲንግ ሲስተም በብላክቤሪ ስልኮች ላይ የሚሰራ ሲሆን የበለጸገውም በ Blackberry Limited Software company በቀድሞው ስሙ Research In Motion (RIM) ነው።

4. Bada

Bada የተባለው የስልክ ኦፕሬቲንግ ሲስተም የተሰራው በሳምሰንግ ኤሌክትሮኒክስ ኩባንያ ሲሆን ከመካከለኛ እስከ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው የሳምሰንግ ስልኮች ላይ ይሰረአል። Bada ስረአተ ክቀና የተጫነባቸው የሳምሰንግ ስልኮች Wave በሚል ስያሜ የሚጠሩ ሲሆን አንድሮይድ የተጫነባቸው የሳምሰንግ ስልኮች Galaxy በሚል ስያሜ ይጠራሉ።

5. Windows Mobile Operating System / Windows OS

ይህንን የስልክ OS ያበለጽገው ማይክሮሶፍት ኩባንያ ሲሆን በማይክሮሶፍት የተሰሩ ስልኮች ና ታብሌቶች ላይ የሚያገለግል ነው።

6. Symbian OS

ሲምቢያን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከአንድሮይድ በፊት በብዛት ስራ ላይ የነበረ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ነበር ፤ በብዛትም ጥቅም ላይ ይውል የነበረው የኖኪያ ስልኮች ላይ ሲሆን አሁንም ድረስ በአንዳንድ ፊቸር ፎኖች ላይ አለ ፤ የተመረተውም Symbian Ltd. በተባል የሶፍትዌር ካምፓኒ ነው።

7. Harmony OS

ሃርሞኒ ኦኤስ በHuawei የተሰራ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ሲሆን ለስማርት ስልኮች፣ ታብሌቶች፣ ለስማርት ቲቪዎች፣ ስማርት ሰዓቶች፣ የግል ኮምፒውተሮች እና ሌሎች ስማርት መሳሪያዎች የሚያገለግል አዲስ ስረአተ ክወና ነው።

8. Magic OS

አንድሮይድን መሰረት አድርጎ የተሰራ ና በሆነር ስልኮች ላይ የሚሰራ ኦኤስ ነው።

ሌሎች አሁን ብዙም የሌሉ ግን በዘመናቸው ለስልክ ና ለሌሎች ዲቫይዞች ያገለግሉ የነበሩ ስረአተክወናዎች

9. MeeGo OS

በኖኪያ ና ኢንቴል ትብብር ዲቭሎፕ የተደረግ ስረአተክወና ሲሆን በተለያዩ ስልክን ጨምሮ በተለያዩ ዲቫይዞች ላይ ይሰራ ነብር ፤ አሁን ግን ብዙም አይታይም።

10. KaiOS

ለጠቅጠቅ ስልኮች ጥቅም ላይ የሚውል ኦፕሬቲንግ ሲስተም ነው።

11. Sailfish OS

ይህ ጆላ በተሰኘ የፊንላንድ የሶፍትዌር አምትራች ካምፓኒ ያበለጸገውን ና ከ2013 ጀምሮ አንድሮይድን እየተወዳደረ ያለ ነው ፤ የአንድሮኢድን አፕሊኬሽኖች እዚህ ላይ መጥቀም እንችላለን።