ለዲጂታል መታወቂያ ለመመዝገብ ምን ያስፈልጋል?|Ethiopian National ID|Fayda Digital ID|Pro...

ለብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ለመመዝገብ አስበው ፤ ይዘውት የሚቀርቡት ማንነትዎን የሚገልጽ ምንም አይነት ማስረጃ ወይም የማረጋገጫ ሰነድ እጅዎ ላይ ከለሌ አይጨነቁ ፤ ከብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ መርሆች መካከል አንዱ አካታችነት/inclusion በመሆኑ ማንም ሰው ሳይመዘገብ እንዳይቀር ታስቦበታል ፤ እርስዎም መመዝገብ ይችላሉ፤ ግን እንዴት? በምን ሁኔታ? ለዚህ መታወቂያ ለመመዝገብ የእድሜገደብ እንደተቀመጠስ ሰምተዋል? ይመለከትዎ ይሆን?ኢትዮጵያውስጥ የሚኖሩ የውጪ ዜጋም ከሆኑ ይህ ዲጂታል መታወቂያ ለርስዎም ትኩረት ሰጥቷል ፤ አንድ ነገር ብቻ ይጠበቅብዎታል እሷን ካሟሉ አለቀ! መመዝገብ ይችላሉ! በክልልም ይሁን በአዲስ አበባ እርስዎ ባሉበት አቅራቢያ የምዝገባ ጣብያ መኖሩን ለማወቅ ቀላል መፍትሄም ተቀምጧል ታድያ ይፍጠኑ እንጂ የእርስዎን ድርሻ ይውሰዱ!