ኢትዮቴሌኮም ግንቦት 2021 ላይ ቴሌብርን ካስተዋወቀን በኋላ ከዳሽንባንክ ና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር የተለያዪ
የፋይናንስ አገልግሎቶችን ይዞልን እንደቀረበ የምናስታውሰው ነው ፤ ይህን አገልግሎት በመጠቀም ያለምንም ማስያዣ ፣ የሰው አይን
ሳይገርፈን በቀላሉ የእጅ ስልካችንን በመጠቀም የብድር አገልግሎት በማግኘት ፍላጎታችንን ማሳካት እንችላለን። መቆጠብም ከፈለግን
በወለድ እንዲሁም ያለወለድ የምንቆጥብበት አማራጭም አለ። ለመሆኑ የቴሌብርን የፋናንስ አገልግሎት ለመጠቀም ምን ቅድመሁኔታዎች
አሉት ፣ ማንም ሰው ለቴሌብር ስለተመዘገበ ብቻ ብድር ማግኘት ይችላልን? እንደ አዲስ ለቴሌብር መመዝገብ ብንፈልግስ በምን መልኩ
መመዝገብ እንችላለን? ምን አይነት አማራጮችስ አሉን? የቴሌብር የደምበኝነት ደረጃችንን እንዴት ማሳደግ እንችላለ? እነዚህን ና
ሌሎች ተያያዥ ተቃሚ መረጃዎችን የያዘውን ቪዲዎ እነሆ!