Ethiopian Tech Laws | computer laws in Ethiopia | Ethiopian Law | Cyber Law in Ethiopia


በሃገራችን ካሉ ቴክኖሎጂ ነክ ህጎች / አዋጆች ፤ ቢያስፈልግዎ!


1. Proclamation No.1072/2018 Electronic Signature Proclamation -- አዋጅ ቁጥር 1072/2018 የኤሌክትሮኒክ ፊርማ አዋጅ
የዚህ ህግ/አዋጅ ዋናው አላማ ለኤሌክትሮኒክ ፊርማ እውቅና መስጠት ና ይህ ፊርማ ያረፈበትን መልዐእክት የሚለዋወጡ ተሳታፊዎችን መብት ና ግዴታ መደንገግ ነው።
2. Proclamation no. 958 Computer Crime -- የኮምፒዩተር ወንጀል አዋጅ ቁጥር 958/2016 GC
የኮምፒዩተር ወንጀልን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር፣ እንዲሁም ለመመርመር እንዲቻል የተዘጋጀ አዋጅ ነው።
3. Electronic Transaction Proclamation 1205/2020 -- የኤሌክትሮኒክ ትራንዛክሽን አዋጅ ቁጥር 1205/2020
ይህ አዋጅ የኤሌክትሮኒክ ንግድን / የኦንላይን ንግድን ወይም አገልግሎት አሰጣጥን የተመለከተ እና እነሱን ለመዳኘት የወጣ የህግ መአቀፍ ነው።
ኦንላይን ስንግዛ ስንሸጥ የተለያዮ መልዕክቶችን ኦንላይን ስንለዋወጥ ችግር ቢያጋጥም በዚህ ና በሌሎች ተያያዥ ህጎች ሊታይ ይችላል።
4) Telecom Fraud offense Proclamation no. 761/2012 -- የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል አዋጅ ቁጥር 761/2012 G.C
ይህ አዋጅ በቴሌኮም ኢንዱስትሪው ላይ እየደረሱ ላሉና የሚደርሱ ጉዳቶችን እንዲሁም የቴሌኮም ማጭበርበን ለመከላክል ና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ነው።
5) National Payment system Proclamation/718/2011 - - የብሔራዊ የክፍያ ሥርዓት አዋጅ 718/2003
ይህ አዋጅ የብሔራዊ የክፍያ ሥርዓትን ለመደንገግ የወጣ አዋጅ ሲሆን ፤ በ 2023 ማሻሻያ ተደርጎበት የብሔራዊ የክፍያ ሥርዓት(ማሻሻያ) አዋጅ ቁጥር 1282/2023 በሚል እንደገና ወጥቷል ።

best websites we must visit | Must know websites |

ለተለያዪ ጉዳዮች የሚጠቅሙን ምርጥ ድረገጾች ፤ ይሞክሯቸው ፡


1. photopea.com
ኮምፒውተራችን ወይም ስልካችን ላይ ምንም አይነት ሶፍትዌር መጫን ሳይጠበቅብን የፎቶ ኢዲቲንግ ና ግራፊክ ዲዛይን ስራ መስራት ያስችለናል ።
2. remove.bg
ከፎቷችን ጀርባ ያለ ማንኛውንም ምስል ለማስወገድ ወይም በፈለግነው ምስል ውይም ከለር ለመቀየር በሰከንድ የሚያስችለን ድረገጽ ነው።
3. circlecropimage.com
ለተለያዩ ጉዳዮች ፎቶ በክብ ቅርጽ መቁረጥ ቢያስፈልገን ፤ በቀላሉ በምንፈልገው መልኩ circle ይቆርጥልናል።
4. storyset.com
ለማስተማሪያነት ወይም የተለያዩ ነገሮችን ለማስረዳት የሚረዱንን ምስሎች ሰርች በማድረግ በምንፈልገው መልኩ አስተካክለን ወይም Customize አድርገን ዳውንሎድ ማድረግ ያስችለናል።ከዚህ በተጨማሪ

የመረጥነውን ምስል customize አድርገን በgif ወይም በቪዲዮ ፎርማትም ዳውንሎድ ማድረግ እንችላለን።
5. pdf24.org
ይህ በጣም የተደራጀ የፒዲኤፍ / pdf solution ነው።
pdf ፋይሎችን edit ማድረግ ፣ መነጠል ፣ የተለያዩ pdf ፋይሎችን ማዋሃድ ፣ pdfን ወደ image ወይም image ወደ pdf መቀየር ፣ pdf ፋይሎችን sign ማድረግ እና የመሳሰሉትን ነገሮች
ምንም አይነት pdf ሶፍትዌር መጫን ሳያስፈልገን ማከናወን ያስችለናል።
6. Quillbot.com
የተለያዩ የእንግሊዝኛ ጽሁፎችን የምናዘጋጅ ከሆነ ፤ የሰዋሰው ፣ የአገላለጽ ና ሌሎችም ችግሮች እንዳያጋጥሙን በሚገባ እርማት ይሰጠናል።
7. diffchecker.com
በተለያዩ ዶክመንቶች ለምሳሌ ፡ በወርድ ፣ በኤክሴል ፣ በቴክስት ዶክመንቶች እንዲሁም በምስሎች መካከል ያለውን ልዩነት ያሳየናል። ዶክመንቱን አፕሎድ በማድረግ ወይም ቴክስቱን ብቻ ፔስት በማድረግ
ልንጠቀምበት እንችላለን።
8. 10minutemail.com
ለተለያዩ ጉዳዮች ጊዜያዊ የኢሜይል አድራሻ ቢያስፈልገን የ10ደቂቃ የኢሜይል አድራሻ ይሰጠናል ፣ ጊዜውን እንደ አስፈላጊነቱ ተጨማሪ ደቂቃዎችን በመጠየቅ ማራዝም እንችላለን።
9. alternativeto.com
ለፈለግነው የስልክ ወይም የኮምፒውተር መተግበሪያ አማራጮችን ከነማብራሪያው ይሰጠናል። ለምሳሌ፡ አንድ በጣም የወደዳችሁት መተግበሪያ ክፍያ ቢጠይቃችሁ ና መክፈል ባትችሉ ፤ ከሱ ጋር ተመሳሳይ አገልግሎት
የሚሰጡ አማራጭ መተግበሪያዎችን ፈልጎ ሊያሳየን ይችላል።