6G | 6th Generation Mobile Network|6ኛው ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ |



6ኛው ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ!

ስድስተኛው ትውልድ በመባል የሚጠራው አዲሱ የሞባይል ኔትዎርክ ቴክኖሎጂ ገና አገልግሎት ላይ ያልዋለ ና በሂደት ላይ ያለ ሲሆን ከ5ኛው ትውልድ (5G) ኔትዎርክ ጋር ሲነጻጸር ከ5G የበለጠ ከፍተኛ ፍጥነት እንደሚኖረው የተገመተ ሲሆን ፤ በቁጥር ለማስቀመጥ ፤ 6ኛው ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ አንድ ቴራ ባይት ዳታ/1024ጊጋ ባይት ዳታ ከአንድ ሰከንድ በታች በሆነ ጊዜ ለማስተላለፍ (ዳውንሎድ ለማድረግ) እንደሚያስችል የሚጠበቅ ሲሆን አሁን እየተጠቀምን ያለነው 5G ኔትወርክ 20GB ዳታ እስክ አንድ ሰከንድ ማስተላለፍ ወይም ዳውንሎድ ማድረግ ያስችላል።

6ኛው ትውልድ ኔትዎርክ የዳታ ፍጥነትን ለመጨመር እጅግ በጣም ከፍተኛ አቅም ያላቸው የሬድዮ ሞገዶችን የሚጠቀም ሲሆን የራሱ ኤአይ ና ማሽን ለርኒንግ ይኖረዋል ተብሏል።

መጪው 6G ኔትወርክ ለ machine to machine/M2M ግንኙነት ወይም ስማርት ዲቫይዞች እርስ በእርስ የሚያደርጉትን ግንኙነት ወይም ለInternet of Things ከ5G በበለጠ እጅጉን የተሻለ እንደሚሆን ተጠቅሷል።

6G ኔትወርክ ለስማርት ከተማ ፣ ለነጂ አልባ ተሽከርካሪዎች(Self Driving Cars) ፣ ለቨርቿል ና ኦውግመንትድ ሪያሊቲ ማርሽ ቀያሪ እንደሚሆን ና በጣም አስተማማኝ ሊያደርጋቸው እንደሚችል ከወዲሁ ተነግሮለታል። 6ኛው ትውልድ ኔትወርክ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2030 ለአገልግሎት ሊደርስ እንደሚችል ይጠበቃል።

How to buy Ethiotelecom shares-Stock market in Ethiopia-Esx-የኢትዮቴሌኮምን አክሲዮን እንዴት መግዛት እንችላለን? Step by Step Guide

የኢትዩቴሌኮምን አክሲዮን በቴሌብር እንዴት መግዛት እንችላለን?



ባሳለፍነው ጥቅምት 06,2017 የአክሲዮን ሽያጭ በመጀመር ከልማት ድርጅትነት ወደ አክሲዮን ማህበርነት የተቀየረው ና ላለፉት 130 ዓመታት ህዝብን ያገለገለው የአንጋፍውን ኩባንያ የኢትዩቴሌኮምን አክሲዮን

በቴሌብር ለመግዛት የሚከተሉትን ሂደቶች ይከተሉ :

የአክሲዮኑን ማመልከቻ ፎርም መሙላት ከመጀመርዎ በፊት የሚከተሉትን ነገሮች ያረጋግጡ :

1. የቅርብ ጊዜ / updated የሆነ telebirr SuperApp መጫንዎን ያረጋግጡ

2. ፎርሙን ስንሞላ ስለሚያስፈልገን የመታወቂያ ሶፍት ኮፒ መያዝ ይኖርብናል : የቀበሌ መታወቂያ ከሆነ የፊት ና የኋላ ገጹን ስካን አድርገን እንያዝ ፤ ፓስፖርት ከሆነ የፊት ገጹ ብቻ በቂ ነው።

3. ክፍያውን ወዲያው ፎርሙን ሲሞሉ ለመክፈል ካሰቡ ቴሌብር አካውንቶ ላይ በቂ ገንዘብ እንዳለ ያረጋግጡ

ከላይ የተዘረዘሩትን ካዘጋጁ ፤ አሁን ፎርሙን መሙላት ይችላሉ :

1. Telebirr SuperApp ላይ በመግባት ፤ የቴሌ አክሲዮን ወይም tele share sales የሚለውን እንምረጥ ፤ ስለ አክሲዮኑ እንዲሁም ስለ ድርጅቱ ዝርዝር መረጃ ማየት ከፈለጉ prospectus ወይም ፕሮስፔክተስን ለማየት የሚለውን ተጭነን በpdf ማንበብ እንችላለን

2. በመቀጠል Book now ወይም ለመግዛት የሚለውን ይጫኑ

3. ፕሮስፔክተስን አንብቤ ተረድቻለሁ እና ደንብና ሁኔታዎችን አንብቤ ተረድቻለሁ የሚሉትን ሁለት ቼክቦክሶች

ክሊክ እናዶርጋቸው / check እናድርጋቸው።

4. አክሲዮን የሚገዙት ለራስ ወይም ለሌላ ከሚለው አንዱን ይምረጡ

5. የሚገዚትን አክሲዮን መጠን ያስገቡ / የመደመር ወይም የመቀነስ ምልክቱን በመጫን መጠኑን ከፍ ና ዝቅ ማድረግ ይቻላል

6. ጠቅላላ ዋጋውን ካዩ በኋላ ቀጣይ ወይም Next የሚለውን ይጫኑ

7. በመቀጠል የግል ወይም ለሌ ሰው የሚሞሉ ከሆነ የሚገዙለትን ሰው መረጃ ያስገቡ

8. መታወቂያዎን ና ፎቶ አፕሎድ ያድርጉ።

9. ቀጣይ ወይም Next የሚለውን ይጫኑ

10. አሁን በማመልከቻችን ላይ ያስገባናቸውን መረጃዎች ካምፓኒው ያጣራል ፤ ማልከቻችን ተቀባይነት ሊያገኝም ላያገኝም ይችላል ፤ ይንንም በSMS ያሳውቃሉ። ያረጋግጡ / confirm የሚለውን ይጫኑ።

11. መቼ እንደሚከፍሉ ይምረጡ ፤ አሁን ይክፈሉ /pay now ወይም በኋላ ለመክፈል / pay later ፤ በኋላ ለመክፈል ከመረጥን ክፍያውን በ48 ሰዓት ውስጥ መክፈል ይኖርብናል ፤ ካልሆነ ማመልከቻችን ውድቅ ይደረጋል።

12. ማመልከቻውን ሞልተን ጨርሰናል !

የኔ አክሲዮን ወይም My shares የሚለውን መርጠን በሂደት ላይ ስለአሉ ፣ ስለተጠናቀቁ ፣ ውድቅ የተደረጉብንን ማመልከቻወች ካሉ ማየት እንችላለን።

Check the video Here / ቪዲዮውን ለመመልከት

መልካም ንባብ!

Password | How to make Strong Password | Password Manager | የይለፍ ቃል | ፓስወርድ |



በስራቦታ ለተለያዮ ሲስተሞች/አፖች ወይም ለ ግል ኢሜይላችን ፣ ፌስቡክ ፣ ትዊተር ፣ ሊንክድኢን ና ለሌሎችም የምንጠቀመው የይለፍቃል / ፓስወርድ ምን መምሰል አለበት?



የይለፍቃል ወይም ፓስወርድ ስንፈጥር በተቻለ መጠን ተገማች ያልሆነ ና በቀላሉ ክራክ ሊደረግ የማይችል መሆን ይኖርበታል፤ፓስወርዳችን በስማችን ወይም በሌሎች በጣም ቀላል በሆኑ ና እኛን የሚያውቁ ሰዎች በቀላሉ የሚገምቷቸው መሆን የለባቸውም።

ፓስወርዳችንን በቃላችን መያዝ ይኖርብናል ፤ ካልሆነ ግን በተገኘው ቦታ ወረቀት ላይ ለማስታወስ ብለን መጻፍ ለደህንነት ስጋት ያጋልጣል! ከዚህ በተጨማሪ የሌሎች ሠዎች ኮምፒውተር ላይ ወይም እንደ ኢንተርኔት ካፌ ያሉ ቦታዎች ላይ ስንጠቀም አልያም ከሌላ ሰው ጋር ኮምፒውተር የምንጋራ ከሆነ የኢሜይል ፣ የፌስቡክ ፣ ወይም የሌሎች ሲስተም ፓስወዶችን ብራውዘር ላይ ሴቭ ማድረግ በጭራሽ የለብንም ፤ ፓሰወርድ ሴቭ አደረግን ማለት ከኛ ውጪ የሆነ ሰው የይለፍቃል ማስገባት ሳይጠበቅበት የኛን መረጃ ሊያይ ሊበረብር ከፍ ሲልም ባልተገባ መልኩ ሊጠቀምበት ይችላል።

ሌላው አንድ አይነት ፓስወርድ ለሁሉም ሲስተም / አፕ መጠቀም ፈጽሞ አይመከርም ምክንያቱም የአንዱ ፓስወርድ ከተገኘ ሁሉም ተጋላጭ ስለሚሆን! የዲክሽነሪ ቃላትን እንደ ፓስወርድ መጠቀም አይመከርም።

ፓስወርድ ለሰዎች ማጋራት / ሼር ማድረግ ጥሩ ባይሆንም የግድ ፓስወርዳችንን ለሌሎች መስጠት ካለብን ግን ከሰጠን በኋላ መቀየር በጣም ጠቃሚ ነው።

የግል መረጃችንን እንደ ፓስወርድ ባንጠቀም በጣም ጥሩ ከመሆኑም በላይ ሀከሮች የግል መረጃችንን ለምሳሌ፡ የልደት ቀን ፣ እድሜ ፣ የጓደኞቻችንን ስም ፣ የምንወዳቸውን እንሰሳት ስም ፤ የትዳር አጋር ስም ፣ የልጆች ስም ና ሌሎችም ከኛ ጋር ትስስ ያላቸውን ነገሮች በተናጠል ወይም እንድላይ አቀናጅቶ በመሞከር ሊያጠቁን ስለሚችሉ ከዚህ እንድንጠበቅም ይረዳናል።

የይለፍ ቃል ስናዘጋጅ ፓስወርዳችን ጠንከር ያለ ግን የምናስታውሰው ሆኖ የሚከተሉትን ነገሮች ማሟላት አለበት ፡

1.) ቢያንስ ስምንት ካራክተር ና ከዚያ በላይ ርዝመት ሊኖረው ይገባል

2.) ፓስወርዳችን ካፒታል ሌተር ፣ ስሞል ሌተር ፣ ስፔሻል ካራክተርስ (ለምሳሌ፡ @ ፣ $ ፣# & ና የመሳሰሉት ማካተት አለበት)

3.) ፓስወርዳችን ለሌሎች ሰዎች ተጋልጧል ብለን ካሰብን ቶሎ መቀየር ይጠበቅብናል ፤ ባለሞያዎች የይለፍ ቃላችንን ቢበዛ በየ ሶስት ወሩ መቀየር እንዳለብን ይመክራሉ።በርግጥ ፓስወርድ በምን ያህል ጊዜ ይቀየር የሚለው ሁሉንም ላያስማማ ይችላል።

መልካም ንባብ!

DeritaTechSolution

Facebook | Telegram | X

CyberSecurity Awareness Month | CyberSecurity |ሳይበር ደህንነት | ሳይበር | What is Cyber? | How to Prevent Cyber Attack



የያዝነው የፈረንጀቹ ጥቅምት ወር/October የCyberSecurity ግንዛቤ መፍጠርያ ወር ነው !



ለመሆኑ ሳይበር ደህንነት/CyberSecurity ምንድነው? አረ ሳይበር / Cyber ብሎ ነገረስ ምንድ ነው?



Cyber / ሳይበር የሚለው ቃል በግርድፉ ሲተረጎም ከኮምፒውተር ወይም ከኮምውተር ኔትወርክ በተለይ ከ ኢንተርኔት ጋር ተዛማጅነት ያለው ወይም ኮምፒውተር ና የኮምፒውተር ኔትዎርክን እንዲሁም ሌሎች የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ውጤቶችን የሚያካትት ማለት ሲሆን ፤ CyberSecurity ማለት ደግሞ ግለሰብን ፣ ድርጅትን ወይም ሃገርን ና መረጃዎቻቸውን ቴክኖሎጂን መሰረት አድርገው ከሚፈጸሙ ጥቃቶች መከላከል ወይም መጠበቅ ነው።

CyberSecurity የሚለው ቃል የተለያዩ ቦታዎች ላይ አንደ አንድ ቃል አንዳንዴም እንደ ሁለት ቃላት (Cyber Security) ተደርጎ ሲጻፍ ይስተዋላል ፤ ነገር ግን እንደ ኢንዱስትሪው ስታንዳርድ ና ትክክሀኛው አጻጻፍ አንድ ቃል ነው ይባላል።

known Smartphone Operating systems|Mobile Operating System Types | Smartphone |የስልክ ስረአተክወናዎች

የስልክ ኦፕሬቲንግ ሲስተም / ስረአተ ክወና አይነቶች



የስልካችን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከስልካችን ጋር እንደልብ መነጋገር እንድንችል ፣ የፈለግነውን አፕሊኬሽን መጫን ና መጠቀም እንድንችል ፣ የስልካችን ሃርድ ዌር ህይወት ዘርቶ መጠቀም እንድንችል ፣ እንደ አስፈላጊነቱ ሚሞሪ መመደብ / Memory allocation and deallocation ፣ ፕሮሰስር ለሚያስፈልጋቸው ፕሮሰሶች መመደብ እና ሌሎችም በርካታ ጥቅሞች አሉት ። ዋና ዋና የስልክ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞችን ስንመለከት ፤

1. Android

ይህ አሁን ላይ በርካታ ስማርት ስልኮች ላይ ተጭኖ የሚመጣ የኦፕሬቲንግ ሲስተም አይነት ሲሆን በጉግል ካምፓኒ የበለጽገም ነው። Android ለእያንዳንዱ አዳዲስ ቨርዥን የተለያየ ስያሜ በመስጠት ይታወቃል። ለምሳሌ ፡ Cupcake(Version 1.5), Donut(version 1.6), Eclair (version 2.0 - 2.1), Oreo(Android version 8.0-8.1), Kitkat (version 4.4) , Vanila Ice cream(Android Version 15) etc.

2. iOS

ይህ Operating system በአፕል ስልኮች ና ሌሎች የአፕል ምርቶች ላይ ለምሳሌ በiPhone , iPad Tablet... ላይ የሚሰራ ነው ፤ ከአንድሮይድ ቀጥሎ የታወቀ ስረአተ ክወና ሲሆን ጠንከር ባለ የደህንነት ፊቸርም ይታወቃል።

3. Blackberry OS

ይህ ኦፕሬቲንግ ሲስተም በብላክቤሪ ስልኮች ላይ የሚሰራ ሲሆን የበለጸገውም በ Blackberry Limited Software company በቀድሞው ስሙ Research In Motion (RIM) ነው።

4. Bada

Bada የተባለው የስልክ ኦፕሬቲንግ ሲስተም የተሰራው በሳምሰንግ ኤሌክትሮኒክስ ኩባንያ ሲሆን ከመካከለኛ እስከ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው የሳምሰንግ ስልኮች ላይ ይሰረአል። Bada ስረአተ ክቀና የተጫነባቸው የሳምሰንግ ስልኮች Wave በሚል ስያሜ የሚጠሩ ሲሆን አንድሮይድ የተጫነባቸው የሳምሰንግ ስልኮች Galaxy በሚል ስያሜ ይጠራሉ።

5. Windows Mobile Operating System / Windows OS

ይህንን የስልክ OS ያበለጽገው ማይክሮሶፍት ኩባንያ ሲሆን በማይክሮሶፍት የተሰሩ ስልኮች ና ታብሌቶች ላይ የሚያገለግል ነው።

6. Symbian OS

ሲምቢያን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከአንድሮይድ በፊት በብዛት ስራ ላይ የነበረ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ነበር ፤ በብዛትም ጥቅም ላይ ይውል የነበረው የኖኪያ ስልኮች ላይ ሲሆን አሁንም ድረስ በአንዳንድ ፊቸር ፎኖች ላይ አለ ፤ የተመረተውም Symbian Ltd. በተባል የሶፍትዌር ካምፓኒ ነው።

7. Harmony OS

ሃርሞኒ ኦኤስ በHuawei የተሰራ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ሲሆን ለስማርት ስልኮች፣ ታብሌቶች፣ ለስማርት ቲቪዎች፣ ስማርት ሰዓቶች፣ የግል ኮምፒውተሮች እና ሌሎች ስማርት መሳሪያዎች የሚያገለግል አዲስ ስረአተ ክወና ነው።

8. Magic OS

አንድሮይድን መሰረት አድርጎ የተሰራ ና በሆነር ስልኮች ላይ የሚሰራ ኦኤስ ነው።

ሌሎች አሁን ብዙም የሌሉ ግን በዘመናቸው ለስልክ ና ለሌሎች ዲቫይዞች ያገለግሉ የነበሩ ስረአተክወናዎች

9. MeeGo OS

በኖኪያ ና ኢንቴል ትብብር ዲቭሎፕ የተደረግ ስረአተክወና ሲሆን በተለያዩ ስልክን ጨምሮ በተለያዩ ዲቫይዞች ላይ ይሰራ ነብር ፤ አሁን ግን ብዙም አይታይም።

10. KaiOS

ለጠቅጠቅ ስልኮች ጥቅም ላይ የሚውል ኦፕሬቲንግ ሲስተም ነው።

11. Sailfish OS

ይህ ጆላ በተሰኘ የፊንላንድ የሶፍትዌር አምትራች ካምፓኒ ያበለጸገውን ና ከ2013 ጀምሮ አንድሮይድን እየተወዳደረ ያለ ነው ፤ የአንድሮኢድን አፕሊኬሽኖች እዚህ ላይ መጥቀም እንችላለን።