እነዚህን ድረገጾች ካላወቁ ወደ ኋላ ቀርተዋል!|Powerful Websites we need to know|Useful websites
በዚህ የቴክኖሎጂ ዘመን ነገሮችን ለማከናወን በጭራሽ መድከም የለብዎትም በቀላሉ ፤ ጊዜን ፣ ገንዘብን እንዲሁም ድካምን መቀነስ የሚችሉባቸው ሁሌም ስራዎን እጅጉን የሚያቀሉ ድረገጾችን ካሉበት አፈላልገን ፣ ፈትሸን በተግባር አቀረብንልዎ ፤ ይሞክሯቸው!
ጉግል ሌንስ|How to use google lens|AI| Machine Learning|Google Lens step by step guide|google Lens|ጎግል
ጉግል/Google Lens ሌንስን ምን ያህል ያውቁታል?
ጉግል ሌንስ የጉግል ካምፓኒ ካበለፀጋቸው የሶፍትዌር ምርቶች መካከል አንዱ ሲሆን AI ና machine learningን በመጠቀም አካባቢያችን ላይ ያሉ ነገሮችን በቀላሉ መረዳት እንድንችል እንዲሁም በስልካችን
ካሜራ ብቻ ፎቶ በማንሳት በርካታ ነገሮችን ማከናወን እንድንችል የሚረዳን የImage recognition tool ነው፤ በለት ተዕለት እንቅስቃሴያችን እጅግ በጣም ጠቃሚ ና አብዛኞቻችን እምብዛም
ያልተጠቀምንበት ነው፤ ጎግል ሌንስን በቀላሉ ስልካችን ላይ ለብቻው ጭነን መጠቀም እንችላለን አልያም google Photos ስልካችን ላይ ካለ እሱ ላይ ልናገኘው እችላለን፤ ኮምፒውተራችን ላይም
Google.com የሚለውን ስንከፍት search box ላይ ያለውን የካሜራ ምልክት ክሊክ በማድረግ ልናገኘው እንችላለን።
Google Lens ከሚሰጠን ጥቅሞች መካከል የተወሰኑትን ስንመለከት :

1. በአካባቢያችን ያሉ ነገሮችን ለምሳሌ ዕፅዋት ፣እንሳት እና የመሳሰሉትን በስልካችን ካሜራ ፎቶ በማንሳት ስማቸውን ጨምሮ ስለ ምንነታቸው ማወቅ ያስችለናል።
2. የትኛውም ፎቶ ወይም ማንኛው ነገር ላይ ያለ text ወይም ፅሁፍ በስልካችን ካሜራ ፎቶ በማንሳት ወደ editable text መቀየር ፣ አማርኛን ጨምሮ ወደ ፈለግነው ቋንቋ መቀየር ፣ ፅሁፉን ኮፒ ማድረግ ወዘተ.
3. ተማሪዎች ወይም መምህራን ከሆንን በየትኛውም የትምህርት አይነት እገዛ ብንፈልግ በሚገባ ይረዳናል።
4. የቆዳ ችግር ካለብን ቦታውን ፎቶ በማንሳት ዝርዝር መረጃዎችን ማግኘት እነችላለን።
5. በየትኛውም ቦታ ያየነውን ነገር ገበያ ላይ ዋጋውን ና መሰል ምርቶችን ማየት ብንፈልግ shopping የሚል አማራጭ አለው እሱን መርጠን አሁንም በጉግል ሌንስ ይቻላል!
Google Lens እነዚህን ና ሌሎችም በርካታ ጥቅሞች ይሰጠናል እንጠቀምበት!
ዝርዘር መረጃ ቢያስፊልግዎ ፤ ቪዲዩዘውን መመልከት ይችላሉ !ቪዲዮውን ለማየት እዚህ ይጫኑ
DeritaTech Solution
Facebook| Telegram| X | Blog
How to type Amharic in windows|Geez numbers|Amharic|አማርኛን በኮምፒውተራችን|ግዕዝ|አማርኛ ፊደላት|Amharic letters
አማርኛን ኮምፒውተርዎ ላይ ለመተየብ ወይም ለመፃፍ ፈልገው ኮምፒውተርዎ ላይ ፓወር ግዕዝ ወይም ሌሎች የአማርኛ መታጻፊያ ሶፍትዌሮችን አጥተው ተቸግረዋል? አሁንም አማርኛን ለመጻፍ ፓወር ግዕዝን አሊያም ኪይ ማን ወይም ሌሎች አማራጮችን እየፈለጉ ከሆነ መረጃ እንስጥዎ ፤ ምን መሰልዎ ማይክሮሶፍት ዊንዶውስ ከዊንዶውስ 7/windows 7/ ጀምሮ አማርኛን ኮምፒውተራችን ላይ የትኛውም ቦታ ላይ ለመፃፍ እንድንችል የአማርኛ መፃፍያ አማራጭ / Amharic input methodን/ አካቶ መጥቷል ፤ በመሆኑም በዚህ ጊዜ አማርኛን ለመፃፍ ምንም ሶፍትዌር መጫን አያስፈልግዎትም! በቀላሉ ከዊንዶውስ ስረዓተ ክወና /Windows Operating System ጋር አብሮ የሚመጣውን አማራጭ መጠቀም ይችላሉ ፤ ፓወር ግዕዝን ስንጠቀም በአብዛኛው የሚሰራልን የኦፊስ ምርቶች ማለትም እንደ ወርድ ፣ ፓወርፖይንት ና ሌሎች የማይክሮሶፍት ምርቶች ላይ እና ሌሎች ውስን ቦታዎች ላይ ብቻ ነው በአንፃሩ ግን ከዊንዶውስ ጋር አብሮ የሚመጣው የፈለግነው ቦታላይ ልንጠቀምበት እንችላለን። ስለዚህ አማርኛ መፃፍ ቢያስፈልግዎ ይህን አማራጭ ይሞክሩት!
ይህን የአማኛ መፃፍያ አማራጭ መጠቀም ከፈለጉ የሚከተለውን ቅደም ተከተል ይከተሉ፤
1) ከ start በተን አጠገብ ያለው መፈለጊያ ላይ language ብለው ይፃፉ
2) በመቀጠል language setting የሚለው ሲመጣ እሱን ክሊክ ያድርጉት
3) Add a language የሚለውን ይምረጡ
4) ከዚያም አማርኛ ወይም Amharic የሚል ይፃፉ ና Next የሚለውን ይምረጡ
5) በመጨረሻም install የሚለውን ይጫኑ ፤ ለበለጠ መረጃ የተያያዘውን የpdf ፋይል ይመልከቱ
ታይፕ ሲያደርጉ አፃፃፉን ማወቅ ከፈለጉ ከታች የተያያዝውን ፒዲ ኤፍ ፋይል ከፍተው ያንብቡት ። Amharic letter typing Guide : https://drive.google.com/file/d/14PTCL0TWIhmLvO5HjyXhGXqkmaK1y_tp/view?usp=sharing ተጨማሪ እገዛ ካስፈለግዎ ፤ በቪዲዎም አዘጋጅተንልዎታል! https://youtu.be/mvYBT0ViU-0

Free english course for Beginners - BBC Learning English-English For Beginners-እንግሊዝኛ ቋንቋ| እንግሊዝኛ ለጀማሪዎች|
እንግሊዝኛንም ይሁን ሌሎች ቋንቋዎችን ለመማር ወይም ያልዎትን እውቀት ለማዳበር ወጪ ማውጣት እሩቅ መጓዝ አይጠበቅብዎትም እጅዎላይ ባለ ስልክ ከቤትዎ ምቾት በቀላሉ መማር ይችላሉ ! ለምንስ ወጪ ያወጣሉ ፤ በዚህ ዘመን? አረ በጭራሽ!
https://youtu.be/7aQHgaiBwm4
የፓስፖርት ዋጋ በጣም ጨመረ -ጉድ ነው!|New Ethiopian Passport Price|Ethiopian Passpor...
የኢትዮጵያ ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከነገ ነሃሴ 01 2016 ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የፓስፖርት አገልግሎት ክፍያ ይፋ አድርጓል ፤ ይህ የአገልግሎት ክፍያ ማሻሻያ የተደረገው የሚንስትሮች ምክርቤት ባጸደቀው ደንብ ቁጥር 550/2024 መሰረት መሆኑም ታውቋል ፤ ለመሆኑ አዲሱ ዋጋ ምን ያህል ይሆን ፤ የትኛውን የፓስፖርት አገልግሎት ይመለከታል? ሙሉ የዋጋ ዝርዝሩን ከነ ማብራሪያው ይመልከቱ።
Subscribe to:
Posts (Atom)