አዲስ አስቸኳይ የስራ ማስታወቂያ ከኢትዮቴሌኮም|New Job opportunity from ethiotelecom|Vaca...

ኢትዮቴሌኮም አዲስ የስራ ማስታወቂያ አውጥቷል ፤ ይህ የስራ እድል ለአዳዲስ ተመራቂዎች እንዲሁም ስራ መቀየር ለሚፈልጉ ሁሉ የቀረበ እድል ሲሆን በርከተ ያሉ ሰራተኞችም ሊቀጠሩበት እንደሚችሉ ይገመታል፤ ለዚህ የስራ ዕድል ለመመዝገብ የቀርቡ ቀላል መስፈርቶች ፣ አስፈላጊ የትምህት ደረጃ፣ መወዳደር የሚችሉ ሰራተኞች ወይም ተመራቂዎች ፣ ለአዲስ አበባ ወይስ ለክልል?የትኞቹ የትምህርት መስኮች? እና ሌሎችም ተያያዥ መረጃዎችን የያዘውን ቪዲዮ ይመልከቱ!

ለዲጂታል መታወቂያ ለመመዝገብ ምን ያስፈልጋል?|Ethiopian National ID|Fayda Digital ID|Pro...

ለብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ለመመዝገብ አስበው ፤ ይዘውት የሚቀርቡት ማንነትዎን የሚገልጽ ምንም አይነት ማስረጃ ወይም የማረጋገጫ ሰነድ እጅዎ ላይ ከለሌ አይጨነቁ ፤ ከብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ መርሆች መካከል አንዱ አካታችነት/inclusion በመሆኑ ማንም ሰው ሳይመዘገብ እንዳይቀር ታስቦበታል ፤ እርስዎም መመዝገብ ይችላሉ፤ ግን እንዴት? በምን ሁኔታ? ለዚህ መታወቂያ ለመመዝገብ የእድሜገደብ እንደተቀመጠስ ሰምተዋል? ይመለከትዎ ይሆን?ኢትዮጵያውስጥ የሚኖሩ የውጪ ዜጋም ከሆኑ ይህ ዲጂታል መታወቂያ ለርስዎም ትኩረት ሰጥቷል ፤ አንድ ነገር ብቻ ይጠበቅብዎታል እሷን ካሟሉ አለቀ! መመዝገብ ይችላሉ! በክልልም ይሁን በአዲስ አበባ እርስዎ ባሉበት አቅራቢያ የምዝገባ ጣብያ መኖሩን ለማወቅ ቀላል መፍትሄም ተቀምጧል ታድያ ይፍጠኑ እንጂ የእርስዎን ድርሻ ይውሰዱ!

አዲሱ የፌደራል ፖሊስ ምን ይዟል?|ኢትዮጵያ|Ethiopian Federal Police| Crime investigatio...

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በቅርቡ ክቡር ጠቅላይ ምንስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ በተገኙበት አንድ አዲስ የስልክ መተግበሪያ ለህዝብ ይፋ አድርጓል ፤ ይህ አዲሱ መተግበሪያ ማንኛውም ሰው የሚያየውን ወይም የሚያጋጥመውን ህግወጥ ድርጊት እንዲሁም ወንጅል የእጅ ስልኩን ብቻ በመጠቀም በፎቶ፣ በቪዲዮ አሊያም በድምጽ ሪፖርት ማድረግ እንዲችል ና ሌሎችንም መረጃዎች ለኢትዮጵያውያን ለማድረስ ያለመ ሲሆን ፤ አካል ጉዳተኞችንም ታሳቢ በማድረግ በምልክት ቋንቋ ጭምር መረጃ ማስተላለፍ እንዲችሉ አድርጓል ። የዚህን አፕ ሙሉ ዳሰሳ በተግባር ከነ ማብራሪያው የያዘውን ቪዲዮ ይመልከቱ! In a move to enhance public safety and security, the Ethiopian Federal Police Commission (EFP), in collaboration with the Artificial Intelligence Institute, launched the ‘EFP Citizen Engagement App’ (EFPApp) at its headquarters in Addis Ababa in the presence of Prime Minister Abiy Ahmed and Deputy Prime Minister Temesgen Truneh.

ከቴሌብር ለመበደር ምን ያስፈልገናል?የቴሌብር ደንበኝነት ደረጃን እንዴት ማሳደግ እንችላለን?Telebirr|Ethio...

ኢትዮቴሌኮም ግንቦት 2021 ላይ ቴሌብርን ካስተዋወቀን በኋላ ከዳሽንባንክ ና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር የተለያዪ የፋይናንስ አገልግሎቶችን ይዞልን እንደቀረበ የምናስታውሰው ነው ፤ ይህን አገልግሎት በመጠቀም ያለምንም ማስያዣ ፣ የሰው አይን ሳይገርፈን በቀላሉ የእጅ ስልካችንን በመጠቀም የብድር አገልግሎት በማግኘት ፍላጎታችንን ማሳካት እንችላለን። መቆጠብም ከፈለግን በወለድ እንዲሁም ያለወለድ የምንቆጥብበት አማራጭም አለ። ለመሆኑ የቴሌብርን የፋናንስ አገልግሎት ለመጠቀም ምን ቅድመሁኔታዎች አሉት ፣ ማንም ሰው ለቴሌብር ስለተመዘገበ ብቻ ብድር ማግኘት ይችላልን? እንደ አዲስ ለቴሌብር መመዝገብ ብንፈልግስ በምን መልኩ መመዝገብ እንችላለን? ምን አይነት አማራጮችስ አሉን? የቴሌብር የደምበኝነት ደረጃችንን እንዴት ማሳደግ እንችላለ? እነዚህን ና ሌሎች ተያያዥ ተቃሚ መረጃዎችን የያዘውን ቪዲዎ እነሆ!