How to type Amharic in windows|Geez numbers|Amharic|አማርኛን በኮምፒውተራችን|ግዕዝ|አማርኛ ፊደላት|Amharic letters

አማርኛን ኮምፒውተርዎ ላይ ለመተየብ ወይም ለመፃፍ ፈልገው ኮምፒውተርዎ ላይ ፓወር ግዕዝ ወይም ሌሎች የአማርኛ መታጻፊያ ሶፍትዌሮችን አጥተው ተቸግረዋል? አሁንም አማርኛን ለመጻፍ ፓወር ግዕዝን አሊያም ኪይ ማን ወይም ሌሎች አማራጮችን እየፈለጉ ከሆነ መረጃ እንስጥዎ ፤ ምን መሰልዎ ማይክሮሶፍት ዊንዶውስ ከዊንዶውስ 7/windows 7/ ጀምሮ አማርኛን ኮምፒውተራችን ላይ የትኛውም ቦታ ላይ ለመፃፍ እንድንችል የአማርኛ መፃፍያ አማራጭ / Amharic input methodን/ አካቶ መጥቷል ፤ በመሆኑም በዚህ ጊዜ አማርኛን ለመፃፍ ምንም ሶፍትዌር መጫን አያስፈልግዎትም! በቀላሉ ከዊንዶውስ ስረዓተ ክወና /Windows Operating System ጋር አብሮ የሚመጣውን አማራጭ መጠቀም ይችላሉ ፤ ፓወር ግዕዝን ስንጠቀም በአብዛኛው የሚሰራልን የኦፊስ ምርቶች ማለትም እንደ ወርድ ፣ ፓወርፖይንት ና ሌሎች የማይክሮሶፍት ምርቶች ላይ እና ሌሎች ውስን ቦታዎች ላይ ብቻ ነው በአንፃሩ ግን ከዊንዶውስ ጋር አብሮ የሚመጣው የፈለግነው ቦታላይ ልንጠቀምበት እንችላለን። ስለዚህ አማርኛ መፃፍ ቢያስፈልግዎ ይህን አማራጭ ይሞክሩት!
ይህን የአማኛ መፃፍያ አማራጭ መጠቀም ከፈለጉ የሚከተለውን ቅደም ተከተል ይከተሉ፤
1) ከ start በተን አጠገብ ያለው መፈለጊያ ላይ language ብለው ይፃፉ
2) በመቀጠል language setting የሚለው ሲመጣ እሱን ክሊክ ያድርጉት
3) Add a language የሚለውን ይምረጡ
4) ከዚያም አማርኛ ወይም Amharic የሚል ይፃፉ ና Next የሚለውን ይምረጡ
5) በመጨረሻም install የሚለውን ይጫኑ ፤ ለበለጠ መረጃ የተያያዘውን የpdf ፋይል ይመልከቱ
ታይፕ ሲያደርጉ አፃፃፉን ማወቅ ከፈለጉ ከታች የተያያዝውን ፒዲ ኤፍ ፋይል ከፍተው ያንብቡት ። Amharic letter typing Guide : https://drive.google.com/file/d/14PTCL0TWIhmLvO5HjyXhGXqkmaK1y_tp/view?usp=sharing ተጨማሪ እገዛ ካስፈለግዎ ፤ በቪዲዎም አዘጋጅተንልዎታል! https://youtu.be/mvYBT0ViU-0