ጉግል ሌንስ|How to use google lens|AI| Machine Learning|Google Lens step by step guide|google Lens|ጎግል

ጉግል/Google Lens ሌንስን ምን ያህል ያውቁታል? ጉግል ሌንስ የጉግል ካምፓኒ ካበለፀጋቸው የሶፍትዌር ምርቶች መካከል አንዱ ሲሆን AI ና machine learningን በመጠቀም አካባቢያችን ላይ ያሉ ነገሮችን በቀላሉ መረዳት እንድንችል እንዲሁም በስልካችን
ካሜራ ብቻ ፎቶ በማንሳት በርካታ ነገሮችን ማከናወን እንድንችል የሚረዳን የImage recognition tool ነው፤ በለት ተዕለት እንቅስቃሴያችን እጅግ በጣም ጠቃሚ ና አብዛኞቻችን እምብዛም
ያልተጠቀምንበት ነው፤ ጎግል ሌንስን በቀላሉ ስልካችን ላይ ለብቻው ጭነን መጠቀም እንችላለን አልያም google Photos ስልካችን ላይ ካለ እሱ ላይ ልናገኘው እችላለን፤ ኮምፒውተራችን ላይም
Google.com የሚለውን ስንከፍት search box ላይ ያለውን የካሜራ ምልክት ክሊክ በማድረግ ልናገኘው እንችላለን።
Google Lens ከሚሰጠን ጥቅሞች መካከል የተወሰኑትን ስንመለከት :

1. በአካባቢያችን ያሉ ነገሮችን ለምሳሌ ዕፅዋት ፣እንሳት እና የመሳሰሉትን በስልካችን ካሜራ ፎቶ በማንሳት ስማቸውን ጨምሮ ስለ ምንነታቸው ማወቅ ያስችለናል።

2. የትኛውም ፎቶ ወይም ማንኛው ነገር ላይ ያለ text ወይም ፅሁፍ በስልካችን ካሜራ ፎቶ በማንሳት ወደ editable text መቀየር ፣ አማርኛን ጨምሮ ወደ ፈለግነው ቋንቋ መቀየር ፣ ፅሁፉን ኮፒ ማድረግ ወዘተ.

3. ተማሪዎች ወይም መምህራን ከሆንን በየትኛውም የትምህርት አይነት እገዛ ብንፈልግ በሚገባ ይረዳናል።

4. የቆዳ ችግር ካለብን ቦታውን ፎቶ በማንሳት ዝርዝር መረጃዎችን ማግኘት እነችላለን።

5. በየትኛውም ቦታ ያየነውን ነገር ገበያ ላይ ዋጋውን ና መሰል ምርቶችን ማየት ብንፈልግ shopping የሚል አማራጭ አለው እሱን መርጠን አሁንም በጉግል ሌንስ ይቻላል!
Google Lens እነዚህን ና ሌሎችም በርካታ ጥቅሞች ይሰጠናል እንጠቀምበት!
ዝርዘር መረጃ ቢያስፊልግዎ ፤ ቪዲዩዘውን መመልከት ይችላሉ !ቪዲዮውን ለማየት እዚህ ይጫኑ
DeritaTech Solution
Facebook| Telegram| X | Blog